ብሔራዊ ደንቦች እና ምክሮች

ምርመራ እና ምልክቶች

የኮሮና ቫይረስ የበሽታ ምልክቶች እንደ ትኩሳት ፣ ሳል ፣ የትንፋሽ እጥረት ፣ ራስ ምታት ፣ ድካም፣ የማሽተት ወይም የጣእም ስሜት ማጣት እና የጡንቻ ህመም ሲሆኑ በተጨማሪም የጉሮሮ ቁስለት፣ የአፍንጫ ፈሳሽ ወይም መደፈን እና ማስነጠስ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ምልክት እንዳለቦት እርግጠኛ መሆን ካልቻሉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡

የበሽታ ምልክቶች ከታዩኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

 • ከታመሙ በቤትዎ ይቆዩ፡፡
 • የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ከታየቦት ምርመራ ያድርጉ።
 • በኮሮና በሽታ ከተያዙ እራሶን ሙሉ በሙሉ ያግልሉ።
 • ከታመሙ እና የህክምና እርዳታ ወይም የከሐኪም ምክር ካስፈለጎ የግል ዶክተርዎን በስልክ ወይም ሌላ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያግኙ፡፡

 የኮሮና ቫይረስ  ምርመራ የት መውሰድ እችላለሁ?

እራስን በመመርመሪያ መንገድ ለራሶ ምርመራ ማድረግ ይችላሉ። ራስን በመመርመሪያ መንገድ በተመረመሩት የምርመራ ውጤት አዎንታዊ መልስ ካገኙ (ኮቪድ-19 ፡ እንዳለዎት የሚያሳይ የምርመራ ውጤት)በኮሚዩናው ውስጥ ባለው የምርመራ ማዕከል ውስጥ የPCR ምርመራ መውሰድ አለብዎት። እንዲሁም ምርመራውን ለማዘዝ የሚኖሩበትን ኮሚዩና ማነጋገር ይችላሉ።

እርሶ ያሉበትን ኮሚዩነው ድረ ገፅ እዚህ ያግኙ። 

ምርመራ ማድረግ መቼ አስፈላጊ ነው?

 • በኮሮና ቫይረስ ተይዣለሁ ብሎ የሚያስብ ማንኛውም ሰው የኮሮና ቫይረስ ምርመራን ማድረግ አለበት፡፡
 • ክትባት ካልወሰዱ እና ኮሮና ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ ምርመራ ማድረግ አለብዎት።
 • ከአንድ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ ምርመራን ማድረግ አለብዎት ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ወይም በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የፍቅረኛኛ ጓደኛ።
 • ራስን በመመርመሪያ መንገድ በተመረመሩት የምርመራ ውጤት አዎንታዊ መልስ ካገኙ ውጤቱን ለማረጋገጥ የPCR ምርመራን እንዲያደርጉ ይመከራል።

የምርመራው ውጤት አዎንታዊ ከሆነ እራሶን ሙሉ በሙሉ ማግለል አለቦት።

በኮሮና በሽታ ከተያዙ ወይም በበሽታው የተያዘ ልጅ ካለዎት ከእርሶ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ስለዚህ ሁኔታ እንዲያሳውቁ እና ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲያበረታቱ ይመከራል።

የኮሮና ምርመራ ውጤት ሲጠብቁ

የኮሮና ምርመራ ውጤትዋን በሚጠብቁበት ጊዜ በሽታው አለመኖሩን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት እስኪያገኙ ድረስ እራስዎን አግልለው ይቆዩ። የምርመራው ውጤት አዎንታዊ ከሆነ እራሶን ሙሉ በሙሉ ማግለል አለቦት።

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ሲኖር የሚደረግ ምርመራ

አሁን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት በሚኖርበት ጊዜ ኳራንታይን ማድረግ አያስፈልግም። ክትባት ያልተከተቡ የቤተሰብ አባላት እና ሌሎች ዘመዶች(የፍቅ ጓደኛ ፣ የቅርብ ጓደኛ ወይም አዳር የሚያድር እንግዳ)በኮሮና በሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካላቸው ለ 7 ቀናት ከሌሎች ሰዎች ጋር ከመገናኘት መቆጠብ ወይም ከዚህ በታች የተብራራውን የምርመራ ሂደት ማካሄድ አለባቸው።

ላልተከተቡ የቤተሰብ አባላት እና ለቅርብ ሰዎች የምርመራ ሂደት 

እርስዎ ወይም ከእርሶ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19
ከተያዙ ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው ተብለው የተመደቡ እና ያልተከተቡ የቤተሰብ አባላት አና የቅርብ የሆኑ ሰዎች በተቻለ ፍጥነት ምርመራ ማድረግ አለባቸው። ከዚያም በኋላ በዚህ መሰረት መመርመር አለብዎት፡

 • በየቀኑ ለ 7 ቀናት እራስን በመመርመሪያ መንገድ

ወይም

 • በየ 2 ቀኑ በPCR ምርመራ (ይህ ምርመራ በኮሚዩናውና ባለው የምርመራ ማዕከል ነው የሚወሰደው)

ምርመራ ላልተከተቡ የቅርብ ግንኙነት ላላቸው ሰዎች

የቤተሰብ አባላት ያልሆኑ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ ቅርብ ያልሆኑ የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የምርመራው ሂደት ማድረግ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ራስን ብራስ በመርመሪያ ዘዴ ወይም በኮሚዩናው ውስጥ ባለው የምርመራ ማዕከል ውስጥ የPCR  ምርመራ እንዲወስዱ ይበረታታሉ።

ይህ ለምሳሌ የሥራ ባልደረቦችዎ ወይም ወደ ከእርሶ ጋር አብረው የሚማሩ የክፍል ተማሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

ክትባት ለወሰደ ወይም በኮቪድ-19  በሽታ ተይዞ ለነበረ

ክትባት ከወሰዱ ወይም ከ 12 ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በኮቪድ-19  ተይዘው ከነበረ ከዚህ በላይ የተብራራውን የኢንፌክሽን ሥርዓት መከተል አያስፈልግዎትም። የኮቪድ-19 ምልክቶችን መከታተል እና ምልክቶች ከታየብዎ ምርመራን ማድረግ አለብዎት። አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙ ራሶን ሙሉ በሙሉ ማግለል አለብዎት።

ሙሉ በሙሉ ራስን ማግለል

አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙ ራሶን ሙሉ በሙሉ ማግለል አለብዎት።

በኮሮና በሽታ ከተያዙ ወይም በበሽታው የተያዘ ልጅ ካለዎት ከእርሶ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ስለዚህ ሁኔታ እንዲያሳውቁ እና ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲያበረታቱ ይመከራል።

እራስን የማግለያን መንገዶች እንዴት መተግበር ይቻላል? 

የኮሮና በሽታ ከያዞት ሙሉ በሙሉ ከሌሎች ሰዎች ራሶን ማግለል ይኖርቦታል። ይህ ክትባት ለወሰዱ ሰዎችም ተግባራዊ ይሆናል።

እራስዎን በቤት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እያገለሉ ከሆነ ከዚህ በታች የሚጠቀሱት መርሆች ይመለከቶታል፥

 • በማንኛውም ጊዜ በቤትዎ መቆየት አለቦት። ከራሶ ቤት ውጪ መውጣት አይችሉም ግን በራስዎ ግቢ ውስጥ ወይም በረንዳ ላይ መሆን ይችላሉ።
 • ወደ መደብሮች መሄድ አይችሉም ፡፡ ሌሎች በሚፈልጉት ነገር ሊረዱዎት ይገባል፡፡
 • አብረዋቸው ከሚኖሯቸው ሰዎች ቢያንስ ሁለት ሜትር ርቀት ሊኖሮት ይገባል፡፡
 • በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ የራስዎ ክፍል እና መታጠቢያ ቤት ሊኖርዎት ይገባል ፡፡ የራስዎን ፎጣ ጨምሮ የራስዎን የመታጠቢያ ቤት መገልገያዎ ዕቃዎች ይጠቀሙ።
 • በቤትዎ ውስጥ ሌሎች እንዳይበከሉ የእጅ ንፅህና ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎት ፡፡ እንዲሁም ሲስሉ ይጠንቀቁ።
 • ቤትዎን በተለይም ብዙ ንክኪ ሚበዛባቸው ቦታዎችን በየጊዤው ያፅዱ ።

እራሶን ሙሉ ለሙሉ ማግላል የሚችሉባቸው ቦታዎች

እራስዎን ሙሉ በሙሉ ማግለል የሚችሉት በቤትዎ፣ ወይም መስፈርቱን በጠበቀ ሌላ ቦታ ላይ ነው።

ኮሚዩናው መስፈርቱን የጠበቀ ራስን ማግላያ ቦታ እንዲኖርዎ የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡ ኮሚዩናው የመኖሪያ ቤቶ ራስን ለማግላል ተስማሚ አይደለም ብሎ ካመነ እራሱ ኮሚዩነው እንደ ሆቴል ወይም ሌላ ራስን የማግለያ ቦታ  ማመቻቸተ አለበት። በነዚህ ጊዜያት ወጪውን ሚሸፍነው ኮሚዩናው ነው።

ራስን የማግላል ጊዜ ሲያበቃ

የመጀመሪያዎቹን የኮሮና ምልክቶች ካዩ 5 ቀናቶች ካለፈ በኋላ እና የትኩሳት መድሃኒት ሳይወስዱ ቢያንስ ለ 24 ሰዓታት ያለ ትኩሳት ከቆዩ ራሶን ማግለልዎን ማቆም ይችላሉ፡፡

የሕመም ምልክቶች ከሌሎት አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙበት ቁን እንስቶ ከ ፭ ቀናት በኋላ ማግለሉን ሊያቋርጡ ይችላሉ። በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን በማግለል ላይ ወይም በኳራንታይን ውስጥ በሚሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥም ራስን ሙሉ በሙሉ ማግለሉ እንዲሁ ያበቃል።

ሙሉ የክትባት መጠን የወሰዱ እና ምንም የበሽታ ምልክት የሌለባቸው ሰዎች ከሁለት ቀናት በኋላ ራሳቸውን ማግለልን ሊያቆሚ ይችላሉ።

በሆስፒታል ውስጥ ላሉ ወይም በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያስተጏጉሉ መድኃኒቶችን ለሚጠቀሙ ሰዎች ራስን የማግለያ ቀኖቹ ሊራዘሙ ይችላሉ፡፡

ስለ ኳራንታይን እና ራስን ስለማግለል ተጨማሪ መረጃ በራስዎ ቋንቋ ከፈለጉ እዚህ ይመልከቱ።

 ጤንነቶ የተጠበቀ ነው ወይም ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስደዋል?

ጤንነቶ የተጠበቀ ነው ተብሎ የሚታሰበው:

 • ሙሉ በሙሉ ክትባት ከወሰዱ፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡
 • አንድ የክትባት መጠን የውሰዱ ከሆነ እና ክትባቱን ከወሰዱ ከ 3 እስከ 15 ሳምንታት ጊዜ ካለፈ። በተጨማሪም ላለፉት አስር ቀናት በኖርዌይ ውስጥ ቆይታ ያደረጉ መሆን አለብዎት፡፡
 • ባለፉት 12 ወራት ውስጥ በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው ከነበረ፡፡

ሙሉ በሙሉ ክትባት ውስደዋል ተብሎ የሚታሰበው:

 • ሁለት የክትባት መጠን የወሰዱ ከሆነ እና የመጨረሻውን የክትባት መጠን ከወሰዱ ከአንድ ሳምንት በላይ ከሆኖት፡፡
 • አንድ የክትባት መጠን ብቻ ያለው ክትባት ከወሰዱ (Janssen), እና ክትባቱን ከተከተቡ ከ3 ሳምንታት ጊዜ በኋላ
 • በኮቪድ-19 ተይዘው ከነበረ እና የኮሮና ቫይረስ አንድ የክትባት መጠን ከአንድ ሳምንት በፊት ወስደው ከነበረ፡፡ አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙ በኋላ ከሶስት ሳምንት ጊዜ በፊት የክትባቱን መጠን መውሰድ አይችሉም፡፡
 • አንድ የክትባት መጠን ከወሰዱ እና ከሶስት ሳምንት በኋላ ባደረጉት የኮሮና ምርመራ አዎንታዊ ውጤት ካገኙ። ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስደዋል ተብሎ የሚታሰበው ራሶን የማግለሎን ሂደት ሲያጠናቅቁ ነው።
 • በደሞ ውስጥ የፀረ ኮቪድ-19 አንቲስቶፍ ከተገኘ እና ከአንድ ሳምንት በፊት አንድ የክትባት መጠን ወስደው ከነበረ።

መሉ በሙሉ ክትባት የወሰዱ ወይም ጤንነቶ የተጠበቀ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ምልክቶችን ካዩ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ክትባት የወሰዱ ወይም ጤንነቶ የተጠበቀ ቢሆንም በኮቪድ-19 ከተያዙ እራስዎን ሙሉ በሙሉ ማግለል አለብዎት።

የኮሮና ክትባት

ክትባቱ ከጠና የኮሮና በሽታ ህመም ይከላከላል። የኖርዌይ የጤና ባለሥልጣናት ክትባቱን መውሰድ የሚችሉትን ሁሉ ሰዎች እንዲወስዱ ይመክራሉ።

የምትኖሩበት ኮሚዩና የኮሮና ክትባትን የመስጠት ኃላፊነት አለበት። ክትባቱ ነፃ እና በፈቃደኝነት የሚወሰድ ነው።

ኖርዌይ ውስጥ ከተወሰነ ጊዜ በላይ የሚቆይ ማንኛውም ሰው የመኖሪያ ሁኔታው ​​ምንም ይሁን ምን ክትባት የማግኘት መብት አለው።

የኖርዌይ የህዝብ ጤና ተቋም (FHI) አሁን ሁሉም ነፍሰ ጡር ሴቶች የኮሮና ቧይረስ ክትባትን እንዲወስዱ ይመክራል።

ክትባት የመውሰድ እድል ካልተሰጠዎት የሚሩበት ኮሚዩናን ያነጋግሩ። በኖርዌይ የጤና አገልግሎቶችን ሲያገኙ አስተርጓሚ የማስመጣት መብት አለዎት።

 የኮሮና ክትባት ለልጆች እና ታዳጊዎች

የ 16 እና የ 17 ዓመት ታዳጊዎች የኮሮና ክትባት እድል እንዲያገኙ ተወስኗል።

ዕድሜያቸው ከ12-15 የሆኑ ልጆችም ክትባት የመውሰድ እድል ይሰጣቸዋል ነገር ግን በመጀመሪያ አንድ የክትባት መጠን ብቻ ይሰጣቸዋል። በዚህ ዕድሜ ላይ ስለሚገኙ ልጆች ክትባት የመጨረሻ ውሳኔ የሚወስኑት ወላጆች ናቸው።

ሊንኩ ሰለ ኮሮና ቫይረስ መረጃ ፊልም ነው። በፊልሙ ውስጥ  ክትባት ምን እንደሆነ ፣ እንዴት እንደሚሰራ እና ለምን እንደምንከተብ መልሶችን ያገኛሉ። 

ክትባት ቢወስዱም እንኳን አጠቃላይ የኢንፌክሽን ቁጥጥር ምክሮችን መከተል አስፈላጊ ነው፡

 • ከታመሙ በቤትዎ ይቆዩ
 • የሕመም ምልክቶች ካሎት ምርመራ ያድርጉ
 • እጅዎን ቶሎ ቶሎ ይታጠቡ

ወደ ውጪ ሀገር ሲሄዱ እና ሲመለሱ

 የሀገር ውስጥ ጉዞ

ሁሉም የሀገር ውስጥ ጉዞዎች መከናወን ይችላሉ። ከታመሙ ወይም ራሶን ሙሉ በሙሉ በማግለል ላይ ከሆኑ መጓዝ የለብዎትም፡፡

በሚጓዙበት ጊዜ ኮሚዩናው የተለያዩ የውስጥ አካባቢያዊ መስፈርተ ሊኖሩት ስለሚችል ከመጓዝዎ በፊት የኮሚዩናውን ድረ ገፅ ይመልከቱ።

የቤት ጉብኝት

ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲሆኑ አጠቃላይ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ምክሮችን መከተል አስፈላጊ ነው። ከታመሙ በቤትዎ ይቆዩ ፣ እጅዎን ቶሎ ቶሎ ይታጠቡ እና ሲያስሉ በክርንዎ ጥግ ላይ ያስሉ። በሚጓዙበት ጊዜ ኮሚዩናው የተለያዩ የውስጥ አካባቢያዊ መስፈርተ ሊኖሩት ስለሚችል ከመጓዝዎ በፊት የኮሚዩናውን ድረ ገፅ ይመልከቱ።

መዋለ ህፃናት እና ትምህርት ቤት

በአከባቢው የኢንፌክሽን ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ኮሚዩናው በትምህርት ቤቶች እና በመዋለ ሕጻናት ውስጥ የትኛውን የእርምጃ መወሰድ እንዳለበት በራሱ መወሰን ይችላል፡፡

ልጆች ከመዋለ ህፃናት ወይም ከትምህርት መቼ በቤታቸው መሆን አለባቸው? ልጅዎ ሲታመም ምን ማድረግ እንዳለበት እዚህ ይመልከቱ፡፡

አዋቂዎች እና ወጣቶች መቼ በቤታቸው መሆን አለባቸው? ሲታመሙ ምን ማድረግ እንዳለብዎ እዚህ ይመልከቱ፡፡