የኮሮና ቫይረስ ለአንዳንድ ቡድኖች የበለጠ አደገኛ ነውን?

Eldre mann og kvinnelig sykepleier

አንዳንድ ቡድኖች ለከባድ የበሽታ ህመም የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው ነገር ግን በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች እንዲሁ ቀላል የበሽታ ምልክቶችን ብቻ ያያሉ፡፡

ለከባድ የበሽታ ህመም የመጋለጥ እድሉ በእድሜ እና በመሰረታዊ በሽታዎች የጨመረ ነው። በተጨማሪም ወንዶች ከሴቶች የበለጠ በከፍተኛነት የመጋለጥ ዕድል አላቸው ፡፡ ያልታወቀ ለከባድ የበሽታ ህመም የሚያጋልጥ ምክንያቶች የሌላቸው ወጣቶችም በበሽታው በከባድ የበሻ ህመም ሊታመሙ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚከሰሰተው ከበስተጀርባ ያሉ በሽታዎች ካሉባቸው ነው ፡፡

ሁሉም ሰው ሰለ ጥሩ የሳል እና የእጅ ንፅህናን ፣ የቅርብ ግንኙነቶችን ብዛት መገደብ ፣ ርቀትን መጠበቅ እና ክትባት ሰለ መውሰድ አጠቃላይ ምክሮችን መከተል አለበት።

በኅብረተሰቡ ውስጥ የኢንፌክሽን መስፋፋት እየጨመረ በሚመጣበት ጊዜ ለከፍተኛ ህመም ተጋላጭ የሚሆኑ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ገለልተኛ አድርገው ቢኖሩ ይመከራል።

  ቀላል ፣ መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ተጋላጭነት?

ለበሽታ ተጋላጭነት ምደባ በቡድን ደረጃ ነው እንጂ በግለሰብ አይደለም ፡፡ በቡድኖቹ ውስጥ ትልቅ የግለሰብ ልዩነቶች ይኖራሉ ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ለከፍተኛ ህመም የመጋለጥ እድልን በተመለከተ የግል ግምገማ ግለሰቡ ከሐኪሙ ጋር በመመካከር ማከናውን አለበት ፡፡

አነስተኛ/የጨመረ መካከለኛ ተጋላጭነት ያላቸው ቡድኖች

 • ዕድሜ 65-69 ዓመት ወይም
 • • ዕድሜው 50-64 ዓመት እና ከዚህ በታች ከሚከተሉት ሥር የሰደደ በሽታዎች አንዱ፡
  • ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ
  • የበሽታ መከላከልን አቅም የሚቀንስ ሕክምና ፣ ለምሳሌ እንደ አነስተኛ በሽታን የመከላከል አቅም ሕክምና
  • የልብና የካርዲዮቫስኩላር በሽታ(በደንብ ከተስተካከለ የደም ግፊት በስተቀር)
  • የጭንቅላት ደም መፍሰስ
  • ከመጠን በላይ ውፍረት (የሰውነት የውፍረት ብዛት ≥ 35kg/m2)
  • የስኳር በሽታ
  • ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ
  • ሥር የሰደደ የሳንባ በሽታ (በደንብ ከተስተካከለ የአስም በሽታ በስተቀር)
  • የመርሳት በሽታ

ዕድሜያቸው ከ 50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎችም በከባድ የኮቪድ -19 በሽታ የመያዝ እድላቸው አነስተኛ ነው። ነገር ግን የሌሎች በርካታ በሽታዎች ጥምረት ያለባቸው አንዳንድ ሰዎች ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ፡፡

ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖች

 • ዕድሜ 70 ዓመት ወይም
 • በመጦሪያ እና እንክብካቤ በማግኛ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ወይም
 • ከዕድሜው ምንም ይሁን ምን አንዳንድ ከባድ የጤና ችግሮች:
  • የሰውነት ክፍል ነቅሎ ተከላ
  • የበሽታ መከላከል አቅም እጥረት
  • ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሄማቶሎጂካል ካንሰር
  • አክቲቭ የካንሰር በሽታ ፣እየተከናወነ ያለ ወይም በቅርቡ የተጠናቀቀ የካንሰር ሕክምና (በተለይም የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንስ ሕክምና ፣ የጨረር ሕክምና ለሳንባ ወይም የኬሞ ቴራፒ)፡፡
  • የመሳል አቅምን የሚቀንሱ የነርቭ በሽታዎች ወይም የጡንቻ በሽታዎች ወይም የሳንባ ኢንፌክሽን (ለምሳሌ ALS ፣ ሴሬብራል ፓልሲ ፣ ዳውን ሲንድሮም)
  • ዳውን ሲንድሮም
  • ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ

ክትባት ለወሰዱ ለበሽታ ተጋላጭ ቡድን ውስጥ ለሚገኙ ግለሰቦች

ሙሉ በሙሉ ክትባት ከተከተቡ በአብዛኛው ከኮቪድ-19 በሽታ እና ከከባድ የበሽታ ህመም ይጠበቃሉ። ስለዚህም ኑሮዎን በኖርማል ሁኔታ መኖር ይችላሉ። የክትባቱ ሙሉ ውጤት ሙሉ በሙሉ ክትባት ከተሰጠ ከ1-2 ሳምንታት በኋላ ይመጣል።

የኖርዌይ የህዝብ ጤና ኢንስቲትዩት በከፍተኛ ሁኔታ የተዳከመ የበሽታ መቋቋም አቅም ያላቸውን ታካሚዎች ሦስተኛውን የኮሮና ቯይረስ ክትባት እንዲወስዱ ይመክራል።

ስለ ሦስተኛው የክትባት መጠን እና ለማን እንደሚተገበር በFHI ገፅ ላይ ያንብቡ (በኖርዌጅኛ)

ክትባት የወሰዱ ሰዎች አጠቃላይ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ደንቦችን መከተል አለባቸው።

ስለ ተጋላጭ ቡድኖች እና ክትባት የበለጠ ያንብቡ (FHI)

አጠቃላይ ምክር ለበሽታ ተጋላጭ ቡድን ውስጥ ላሉ ሰዎች እና ለቤተሰቦቻቸው

የሚያስፈልጎት መድሃኒትቶች እንዳሎት ያረጋግጡ። በቋሚነት የሚወስዱዋቸውን መድሃኒቶች መውሰድ ይቀጥሉ። ከሐኪምዎ ጋር በመመካከር ብቻ ለውጦችን ያድርጉ።

 • የጤና ክትትል ቀጠሮዎች እና ምርመራዎች ካሎት ከሚያክሞት ሰው ሌላ መልእክት እስካልተቀበሉ ድረስ ቀጠሮዎን መጠበቅ አለብዎት። ጥርጣሬ ካለዎት ሐኪምዎን ያነጋግሩ።
 • ጥሩ የእጅ እና የሳል ንፅህናን መጠበቅ ያስታውሱ። ይህ ደግሞ አብረዋቸው ለሚኖሩ እና ለጉብኝት የሚመጡ ሰዎችንም ይመለከታል። ቤቶን ውስጥ አዘውትረው ያፅዱ ፣ በተለይም በተደጋጋሚ የሚነኩዋቸው ቦታዎች።
 • በሥራ ፣ በውጭም ሆነ በሌሎች በሚቆዩባቸው ቦታዎች ከሌሎች ሰዎች ርቀቶን ይጠብቁ።
 • አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩ ነው ሆኖም ግን መጨናነቅ የሌለባቸውን ቦታዎች ይምረጡ።
 • የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምልክቶች ካላቸው ሰዎች ጋር ግንኙነትን ያስወግዱ።

የሚቻል ከሆነ የሕዝብ መጓጓዣን አጠቃቀሞን ይገድቡ ፣ በተለይም ሰው በሚበዛበት ሰዓት።

አጠቃላይ ምክር ለቤተሰብ

አጠቃላይ ምክር በበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች ውስጥ ላሉ ሰዎች ቤተሰቦች :

 • ለበሽታው ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ማህበራዊ ግንኙነቶን አያቋርጡ።
 • በበሽታው የመያዝ እድልን ለመቀነስ አሁን ያሉትን የንፅህና አጠባበቅ ምክሮች እና ሌሎች ምክሮችን ይከተሉ፡፡
 • የመተንፈሻ አካላት ላይ ምልክቶች ካዩ ወይም ሙሉ በሙሉ ጥሩ ስሜት ካልተሰማዎት ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን አይጎበኙ፡፡
 • አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እገዛን ያድርጉ፡፡
 • ለበሽታው ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር አብረው የሚኖሩ ከሆነ እና የመተንፈሻ አካላት ላይ የመያዝ ምልክቶች ካዩ ወይም ጥሩ ስሜት የማይሰማዎት ከሆነ ግንኙነትዎን ይገድቡ። ከተቻለ በተናጥል ክፍሎች ውስጥ እንዲቆዩ እና እንዲተኙ በተጨማሪም የተለየ መታጠቢያ ቤትን እና መጸዳጃ ቤቶችን እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ርቀትን መጠበቅ እና የግል ፎጣዎች እና የመታጠቢያ ቤት እቃዎች በመታጠቢያ ቤት እና በመፀዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

 ከታመሙ ምን ያድርጉ?

ህመም የሚሰማዎት ከሆነ እና በኮሮና ቫይረስ ተይዛሉው ብለው ካሰቡ ወድያውኑ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ያነጋግሩ፡፡ እንደ ትኩሳትና ሳል ያሉ ምልክቶች ካዩ እንዲሁም የትንፋሽ እጥረት ካጋጠሞ እና በአጠቃላይ የጤነቶ ሁኔታ ከቀነሰ ለምርመራ የአከባቢውን የጤና አገልግሎት ማነጋገር አለብዎት ፡፡

በሌላ መንገድ ዶክተርን የሚያነጋግሩባቸው ሌሎች አጣዳፊ የህመም ምልክቶች ካዩ በቫይረሱ ​​ቢያዙም የይያዙም የጤና አገልግሎቱን ማነጋገሩ አስፈላጊ ነው ፡፡

በተጋላጭ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ሰዎች የሕክምናን ሂደታቸውን መቀየር አለባቸው?

የጤና ክትትል እና ምርመራ ቀጠሮ ካሎት ቀጠሮውን አይሰርዙ። ሐኪምዎን ሳያማክሩ  በሕክምናዎ ላይ እየወሰዱ ያሉትን መድኃኒቶች እንዲለውጡ አንመክርም ፡፡ መሠረታዊው በሽታዎችን በደንብ መከታተል እና መታከም አስፈላጊ ነው። ስለ ህክምናዎ ጥያቄዎች ካሉዎት ሀኪምዎን ያነጋግሩ ፡፡

ምክር በተጋጭ ቡድኖች ውስጥ ላሉ እና ለተከተቡ ሰዎች

ሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ከኮቪድ-19  ቫይረስ እና ከከባድ የበሽታ ህመም በአብዛኛው ሁኔታ የተበቁ ናቸው። ስለዚህ ኑሮዋቸውን በመደበኛነት መቀጠል ይችላሉ፡፡ የክትባቱ ሙሉ ውጤት ሙሉ ክትባት ከተወሰደ ከ 1-2 ሳምንታት በኋላ ይመጣል. መከላከያው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን አናውቅም ፡፡ የክትባቱ መከላከያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከቀነሰ እዲስ የክትባት መጠን መውሰድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ክትባት የወሰዱ ሰዎች አጠቃላይ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ደንቦችን መከተል አለባቸው ፡

 (FHI)ለበለጠ መረጃ ስለ ተጋላጭ ቡድኖች እና ክትባ ያንብቡ (FHI)

በተጋላጭ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ህፃናት እና ወጣቶች

ተለምዶው እንደሚያሳየው ልጆች በኮቪድ ከባድ ህመም እንደሚይዙ እና በአብዛኛውን ጊዜ ሆስፒታል መተኛት እንደሌለባቸው ያሳያል፡፡ ይህ ሥር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ሕፃናትም ጨምሮ ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ -19 ምክንያት  በልጆች ላይ ሞት የተከሰተው  በጣም ጥቂት ሲሆን እንዲሁም በጤናማ ልጆች ላይ ደግሞ በጣም አናሳ ነው ፡፡

የልጆች ትምህርት ቤት እና ኪንደርጋርደን ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች

አንዳንድ ከባድ ህመም ያላቸው ልጆች አሉ እነዚህ ደግሞ ለበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለለዚህም በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ ልጆች የተመቻቸ ትምህርትን መስጠት ከግምት ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ በመሠረቱ፣ ይህ የሚደረገው ያልተለመዱ እና ከባድ በሽታዎች ላላቸው ልጆች ነው፡፡