ጉዞ ወደ ኖርዌይ

ጉዞ ወደ ኖርዌይ

በአውሮፓ ሀገሮች ውስጥ የሚመለከተውን መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ 
Re-open EU (europa.eu)

ወደ ኖርዌይ ማን መጓዝ ይችላል?

ወደ ኖርዌይ ማን መጓዝ እንደሚፈቀድለት ህግ ላይ አንዳንድ ገደቦች አሉ።

ወደ ኖርዌይ መጓዝ የሚችሉት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት ሲያሟሉ ነው፡

 • ተቀባይነት ያለው ሙሉ በሙሉ ክትባት እንደወሰዱ የሚያሳይ የኮሮና ክትባት የምስክረነት ወረቀት ማስመዝገብ የሚችሉ ወይም ባለፉት ስድስት ወራት የኮሮና ቫይረስ ይዞት አነደነበ ማስረጃ ያላቸው።
 • በአውሮፓ ህብረት EU/EØS ፣ በስዊዘርላንድ ፣ በኢንግላንግ ወይም በሀምራዊ ሀገር/ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እና ላለፉት 10 ቀናት በዛው የቆዩ ወደ ኖርዌይ መጓዝ ይችላሉ።

ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱ ቡድኖች በአንዱ ውስጥ የማይካተቱ ከሆነ ወደ ኖርዌይ ለመጓዝ ከዚህ በታች ባለው በአን ልዩ ሁኔታ ሥር መካተት አለብዎት።

 የሚጓዙበት ሀገር ምን አይነት ቀለም አለው?

እርስዎ የሚጓዙበት ሀገር ቀለም ኳርንታይን ማድረግ እንዳለቦት ወይም እንደሌለቦት እና ወደ ኖርዌይ ሲገቡ የትኞቹን ህጎች መከተል እንዳለብዎት ይወስናል። የሚጓዙበት ሀገር ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ውስጥ ምን ዓይነት ቀለም እንዳለው ይመልከቱ። የአገሮቹን ዝርዝር እዚህ ማግኘት ይችላሉ ፣ ይዘቱ በእንግሊዝኛ ነው።

የሀገሪቱ ቀለም ምን እንደሆነ ካወቁ በኋላ ፣ የትኞቹ ህጎች ለእርስዎ እንደሚተገበሩ እዚህ ማንበብ ይችላሉ 

ለእርስዎ ምን ይሠራል?

 • ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስጃለሁ ወይም ባለፉት ስድስት ወራት በኮቪድ-19  ተይዤ ነበር ይህንንም በኮሮና የምስክር ወረቀት ማረጋገጥ እችላለሁ። 

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በኮቪድ ከተያዙ ወይም ሙሉ በሙሉ ክትባት ከወሰዱ (ሚቆጠረው ምርመራውን ከሰጡበት ቀን ጀምሮ፣ ራስን የማግለያውን ጊዜ ጨርሰው መሆን አለበት)እና ይህንን በትክክለኛ የኮሮና የምስክር ወረቀት ማረጋጥ ከቻሉ ከጉዞ ኳራንታይን ነፃ ነዎት።

እንዲሁም የጉዞ ምዝገባ ፎርምን መሙላትም ሆነ በድንበሩ ላይ ምርመራ መውሰድ አያስፈልግዎትም።

 • ዕድሜዬ 18 ዓመት በታች ነው

ከግራጫ ሀገሮች እና አካባቢዎች ወደ ኖርዌይ የመግባት መብት ያለው ማን እንደሆነ አሁንም አንዳንድ ገደቦች አሉት። ይህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችንም ይመለከታል። በ UDI ድረ ገፅ ላይ ይህ ማንን እንደሚመለከት አጠቃላይ እይታ ያገኛሉ።

አረንጓዴ ወይም ብርቱካን ያልሆነ አካባቢ/ሃገር

ከቀይ ፣ ጥቁር ቀይ ወይም ሐምራዊ ሀገር ወይም አካባቢ ከተጓዙ ወደ ኖርዌይ ጉዞን ማድረግ ይችላሉ።

ከግራጫ ሀገር ወይም አካባቢ ወደ ኖርዌይ የመግባት መብት ያለው ውስን ሰው ነው።.  ይህ የትኛዎቹን ሀገሮች እንደሚመለከት እዚህ ይመልከቱ።

የሚከተሉት ደንቦች ይተገበራሉ:

 • ዕድሜያቸው ከ 16 ዓመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች የጉዞ መመዝገቢያ ቅጽን መሙላት አለባቸው። ቅጹ ዲጂታል ነው እና ከመግባቶ ከ 72 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሊሞላ ይችላል።
 • በድንበር ላይ ሲደርሱ ምርመራ ማድረግ አለብዎት። ጉዞዎን ከመቀጠልዎ በፊት በአንትጅን ፈጣን ምርመራ የተውሰደው የምርመራ ውጤት እኪደርስ ድረስ መጠበቅ አለብዎት። ፈተናውን ለመውሰድ አስቸጋሪ ከሆነ ፣ ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች አይገደዱም ፣ ይህ ውሳኔ ምርመራው በሚወሰድበት ቦታ ይወሰናል።
 • በጉዞ ኳራንታይን ውስጥ መሆን የለብዎትም። ኖርዌይ ከደረሱ ከ 3 ቀናት በኋላ የ PCR ምርመራ እንዲወስዱ ይመከራል።

አረንጓዴ ወይም ብርቱካናማ ሀገረር ወይም አካባቢ

የሚከተሉት ደንቦች ከአረንጓዴ ወይም ብርቱካንማ ሀገሮች ወይም አካባቢዎች ለሚጓዙ ይተገበራሉ:

 • ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የጉዞ ምዝገባ ቅጽ መሙላት የለባቸውም።
 • ድንበር ላይ ሲደርሱ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግዎትም።
 • የጉዞ ኳራንታይን ውስጥ መግባት የለብዎትም።
 • ከአረንጓዴ ወይም ብርቱካንማ ሀገር ወይም አካባቢ እየተጓዝኩ ነው

የትኞቹ አገሮች አረንጓዴ እና ብርቱካን እንደሆኑ እዚህ ይመልከቱ።

ከአረንጓዴ እና ብርቱካናማ ሀገሮች ወይም አካባቢዎች የ ሚመጡ ተጓዦች ሁሉ በጉዞ ኳራንታይ ውስጥ መሆን የለባቸውም ፣ በሚደርሱበት ቦታ ምርመራ ማድረግ የለባቸውም እና ለመግባት የምዝገባ ቅጽ መሙላት አያስፈልጋቸውም። ይህ የኮሮና የምስክር ወረቀት ከሌለዎትም ተግባራዊ ይሆናል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በኮቪድ -19 ከተያዙ ወይም ሙሉ በሙሉ ክትባት ከወሰዱ ይህንን ተቀባይነት ባለው የኮሮና የምስክር ወረቀት ማስመዝገብ አለብዎት።

 • ከቀይ ጥቁር ቀይ ወይም ሐምራዊ ሀገር ወይም አካባቢ እጓዛለሁ ነገር ግን ክትባት አልወሰድኩም ወይም ባለፉት ስድስት ወራት በኮቪድ-19 አልተያዝኩም

የትኞቹ ሀገሮች ቀይ እንደሆኑ እዚህ ይመልከቱ።

ወደ ኖርዌይ ሲገቡ የሚከተሉት ህጎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡

 • የጉዞ መመዝገቢያ ቅጽን መሙላት አለቦት። ቅጹ ዲጂታል ነው እናም ከመግባቶ ከ 72 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሊሞላ ይችላል። ቅጹን እዚህ ማግኘት ይችላሉ።
 • በድንበር ላይ ሲደርሱ ምርመራ ማድረግ አለብዎት። ይህ  የአንትጅን ፈጣን ምርመራ  ነው። የተውሰደው የምርመራ ውጤት እኪደርስ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።  አንዳንድ ከዚህ ህግ ነፃ የሆኑ አሉ ፣ እዚህ ይመልከቱ።
 • የጉዞ ኳራንታይን ማድረግ አለቦት። የጉዞ ኳራንታይኖን በራስዎ ቤት ወይም በሌላ ተስማሚ ማረፊያ ቦታ ሊያከናውኑ ይችላሉ። ለመቆየት ተስማሚ ቦታ ከሌለዎት ፣ ሲደርሱ በኳራንታይን ሆቴል ለመቆየት እድል ይሰጦታል። ዋናው ደንብ የጉዞ ኳራንታይኑ ለ10 ቀናት ጊዜ የሚቆይ ነው።
 • የኳራንታይን ምርመራ:
  • ኖርዌይ ከደረሱ ከሶስት ቀናት በኋላ የPCR ምርመራ መውሰድ ይችላሉ ፣ ምርመራውን ለመውሰድ እራስዎ ኮሚዩና ቤቱን ማነጋገር አለብዎት። የምርመራው ውጤት አሉታዊ ከሆነ ፣ የጉዞ ኳራንታይኑን ማቆም ይችላሉ። የምርመራ ውጤቱን በማስረጃ መመዝገብ መቻል አለበት።
 • EØS ከስዊዘርላንድ እና ከእንግሊዝ ውጭ ግራጫ ከሆነ ሀገር ነው የምጓዘው ነገር ግን ክትባት አልወሰድኩም ወይም ባለፉት ስድስት ወራት በኮቪድ ፡፩፱ አልተያዝኩም።

ከEØS፣ ከስዊዘርላንድ እና ከዩናይትድ ኪንግደም ውጭ ከሆኑ ግራጫ ሀገራት ወደ ኖርዌይ የመግባት መብት ያለው ውስን ሰዎች ናቸው ፣ በUDI  ላይ ይህ ማን እንደሚመለከት አጠቃላይ እይታ ያገኛሉ።

ወደ ኖርዌይ እንዲገቡ ከተፈቀደልዎት የሚከተለው ይተገበራል:

 • የጉዞ መመዝገቢያ ቅጽን መሙላት አለቦት። ቅጹ ዲጂታል ነው እናም ከመግባቶ ከ 72 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሊሞላ ይችላል።
 • በድንበር ላይ ሲደርሱ ምርመራ ማድረግ አለብዎት። ይህ  የአንትጅን ፈጣን ምርመራ  ነው። የተውሰደው የምርመራ ውጤት እኪደርስ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።  አንዳንድ ከዚህ ህግ ነፃ የሆኑ አሉ ፣ እዚህ ይመልከቱ።
 • የጉዞ ኳራንታይን ማድረግ አለቦት። የጉዞ ኳራንታይኖን በራስዎ ቤት ወይም በሌላ ተስማሚ ማረፊያ ቦታ ሊያከናውኑ ይችላሉ። ለመቆየት ተስማሚ ቦታ ከሌለዎት ፣ ሲደርሱ በኳራንታይን ሆቴል ለመቆየት እድል ይሰጦታል። ዋናው ደንብ የጉዞ ኳራንታይኑ ለ10 ቀናት ጊዜ የሚቆይ ነው።
 • የኳራንታይን ምርመራ:
 • ኖርዌይ ከደረሱ ከሶስት ቀን በኋላ የPCR ምርመራ መውሰድ ይችላሉ ፣ ምርመራውን ለመውሰድ በኳራንታይን ሆቴል ውስጥ እድል ይሰጥዎታል። ምርመራው አሉታዊ ከሆነ ፣ ከጉዞ ኳራታይኑ መውጣት ይችላሉ። አሉታዊ የምርመራ ውጤትን በማስረጃ ማቅረብ መቻል አለብዎት።

ወደ ኖርዌይ ለሚጓዙ የውጭ ዜጎች የኮሮና የምስክር ወረቀት

ሙሉ በሙሉ ክትባት ከወሰዱ ወይም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ኮሮና ይዞት ከነበረ እና ይህንን ከአውሮፓ ህብረት የኮሮና ምስክር ማረጋገጫ መፍትሄ ጋር በተገናኘ በተረጋገጠ የኮሮና የምስክር ወረቀት በኩል ሰነድ ከሰጡ ከየትኛውም ሀገር ቢጓዙ ወደ ኖርዌይ በነፃነት መጓዝ ይችላሉ። ከጉዞ ኳራንታይን፣ ከጉዞ በፊት ከሚደረግ ምርመራ ፣ ድንበር ላይ ከሚደረግ ምርመራ እና ከመግባቶ በፊት ከሚሞላ የጉዞ መመዝገቢያ ቅጽ ነፃ ኖት።

ኖርዌይ ሙሉ ለሙሉ ክትባት የወሰደ ብላ የምትጠቀምበት ትርጓሜ:

 • 2 የክትባት መጠን የወሰደ ፣ እና የመጨረሻው የክትባት መጠን ከተወሰደ ከ 1 ሳምንት በላይ ከሆነ።
 • አንድ የክትባት መጠን ብቻ ያለውን ክትባት የተከተበ እና ክትባቱ ከተወሰደ ከ 3 ሳምንታት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
 • በኮቪድ-19 ተይዘው ከነበረ እና የኮሮና ቫይረስ አንድ የክትባት መጠን ከአንድ ሳምንት በፊት ወስደው ከነበረ ፡፡ አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙ በኋላ ከሶስት ሳምንት ጊዜ በፊት የክትባቱን መጠን መውሰድ አይችሉም፡፡
 • አንድ የክትባት መጠን ከወሰዱ እና ከሶስት ሳምንት በኋላ ባደረጉት የኮሮና ምርመራ አዎንታዊ ውጤት ካገኙ። ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስደዋል ተብሎ የሚታሰበው ራሶን የማግለሎን ሂደት ሲያጠናቅቁ ነው።
 • በደሞ ውስጥ የኮቪድ የአንቲ ስቶፍ ከተገኘ እና ከአንድ ሳምንት በፊት 1 የክትባት መጠን ከወሰዱ።

የየትኞቹ አገሮች የኮሮና ምስክር ወረቀት በኖርዌይ ተቀባይነት እንደሚያገኝ በ rejeringen.no  ተጨማሪ ያንብቡ።

ወደ ኖርዌይ ከመግባት በፊት የሚደረግ የጉዞ ምዝገባ

ከቀይ ፣ ጥቁር ቀይ ፣ ሐምራዊ እና ግራጫማ ሀገሮች እና አካባቢዎች የሚመጡ ተጓዦች ወደ ኖርዌይ ከመግባታቸው በፊት የጉዞ ምዝገባ ቅጽ መሙላት አለባቸው። ቅጹ በዲጂታል መልክ መሞላት አለበት። ምዝገባውን ከጨረሱ በኋላ ፣ ሲደርሱ ለፖሊስ የሚያሳዩት ደረሰኝ ይደርስዎታል። ምዝገባው ጉዞ ከመጀመሮ ከ 72 ሰዓታት ቀደም ብሎ ሊሞላ አይችልም።

እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ዲጂታል የመግቢያ ምዝገባውን ይመልከቱ (entrynorway.no)

ቅጹን ለመሙላት ለእገዛ ካስፈለጎት በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ+47 33 41 28 70 መደወል ይችላሉ። ወይም ደግሞ ወደዚህ አራሻ ኢሜል ይካኩ support@entrynorway.no

የስልክ አገልግሎቱ በየቀኑ 24 ሰዓት ክፍት ነው ፡፡ ከ 08:00-22:00 ባለው ሰዓት መመሪያ በፖላንድ ፣ ራሽያኛ ፣ ሊቱዌኒያ እና ሮማኒያኛ ይሰጣል።

የትኞቹ የኳራንታይን ህጎች ለእርስዎ እንደሚተገበሩ በዚህ ድህረ ገዕ ላይ ይመልከቱ (Helsedirektoratet.no)

ወደ ኖርዌይ ከመግባቶ በፊት የሚደረግ ምርመራ

ከቀይ ፣ ጥቁር ቀይ ፣ ሐምራዊ እና ግራጫማ ሀገሮች እና አካባቢዎች የሚመጡ ተጓዦች ወደ ኖርዌይሲደርሱ ወዲያውኑ የኮቪድ-19  ምርመራ መውሰድ አለበት።

በቂ ምክንያት የሌላቸው ሰዎች፣ ላለመመርመር ፈቃደኛ ያልሆኑ ሃገሪቱዋን በፈቃደኝነት ለቀው ይሄዳሉ ወይም ቅጣት ይቀጣሉ።

በአውሮፕላን ማረፊያው ወይም በአገሪቱ ውስጥ በሚደርሱበት ቦታ ምርመራውን መውሰድ አለብዎት። ፈተናው የአንቲጂን ፈጣን ምርመራ መሆን አለበት። የምርመራውን ውጤት እስኪያገኙ ድረስ በቦታው ላይ የመጠበቅ ግዴታ አለብዎት ፡፡

አዎንታዊ የምርመራ ውጤት በሚከሰትበት ጊዜ በ 24 ሰዓታት ውስጥ የPCR ምርመራ ማድረግ አለቦት። ነገር ግን ከEØS/ስዊዘሪላንድ አከባቢ ውጪ ከሆነ ቆይታ ያደረጉት እና የምርመራዎ ውጤት ኤዎንታዊ ከሆነ በቦታው ላይ የPCR ምርመራ ማድረግ አለብዎት፡፡

የጉዞ ኳራንታይን

ከቀይ ፣ ጥቁር ቀይ ፣ ሐምራዊ እና ግራጫማ ሀገሮች እና አካባቢዎች ወደ ኖርዌይ የሚመጣ ተጓዥ በዋነኛነት ለ10 ቀናት በኳራንታይን መቆየት ይኖርበታል። ህጉ ልዩ ሁኔታዎች አሉት እነሱህን እዚህ ይመልከቱ።

የጉዞ ኳራንታይን በቤቶ ውስጥ ወይም በሌላ ተስማሚ የመኖሪያ ቦታ መከናወን አለበት። የጉዞ ኳራንታይኑን ለማካሄድ ሌላ ተስማሚ ማረፊያ ከሌለዎት የኳራንቲን ሆቴል ሊሰጥዎት ይችላል።

ወደ ኖርዌይ ሲጓዙ በአረንጓዴ ወይም ብርቱካንማ ሀገር ወይም አካባቢ የሚጓዙ ከሆነ በዚያ አገር ውስጥ በቆዩበት ጊዜ ልክ የኳራንታይን ጊዜው ያጥራል።

የጉዞ የኳራንታይን ውስጥ ከሆኑ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት:

 • የኳራንታይን ጊዜን በቤቶ ወይም በሌላ ተስማሚ ቦታ ማሳለፍ አለብዎት።
 • ወደ ሥራ ፣ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ኪንደርጋርደን አይሂዱ፡፡
 • የህዝብ መጓጓዣ ትራንስፖርቶችን አይጠቀሙ፡፡ ከEØS ፣ ከስዊዘርላንድ ወይም ከዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ወደ ኳራንታይን ስፍራ ሲጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርቶችን መጠቀም ይችላሉ ፣ ወይንም ደግሞ በተቃራኒው መንገድ ካራንታይኑ ከማብቃቱ በፊት ኖርዌይን ለቀው ከሄዱ ፡፡ ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የፊት ማስክ መጠቀም አለባቸው።
 • እንደ ሱቆች ፣ ፋርማሲዎች እና ካፌዎች ያሉ የህዝብ ቦታዎችን አይጎበኙ ፡፡ ሌሎች አማራጮች ከሌሉዎት ወደ መደብር ወይም መድኃኒት ቤት አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች መሄድ ይችላሉ። ከሌሎች ጋር ደህንነቱ የጠበቀ ርቀት እንዳሎት ያረጋግጡ፡፡
 • ጎብኝዎች እይኑርዎት፡፡

የኳራንታይንን ግዴታ መጣስ ያስቀጣል።

በጉዞ ኳራንታይን ላይ ሳሉ የሚደረግ ምርመራ

ኖርዌይ ከደረሱ ከሶስት ቀናት በኋላ የPCR ምርመራ ከወሰዱ እና የምርመራው ውጤት አሉታዊ ከሆነ የጉዞ ኳራንታይንኑን ማቆም ይችላሉ። የምርመራውን ውጤት በሰነድ ማስመዝገብ መቻል አለብዎት። ይህ ለምሳሌ የምርመራ ውጤቶች በሚታይበት በHelsenorge.no ገጽ ላይ ሊሆን ይችላል።

በኳራንታይን ሆቴል ውስጥ ከቆዩ ኮሚዩናው ምርመራ እነዲወስዱ ያመቻቻል።

ከጉዞ ኳራንታይን ህግ ልዩ መርሆች

ከጉዞ ኳራንታይን ህግ ልዩ መርሆች አሉ። አንዳንዶቹ ልዩ መርሆች በሥራ እና በመዝናኛ ጊዜ ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን ሌሎች ልዩ ሁኔታዎች ደግሞ በሥራ ሰዓት ላይ ብቻ ይተገበራሉ።

የእርስዎን ሁኔታ ሊያካትት የሚችሉት ልዩ ሁኔታ ካለ የስራ ቀጣሪዎን ያነጋግሩ። ለምሳሌ:

 • በረጅም ርቀት መጓጓዣ ውስጥ የሚሰሩ የባለሙያ አሽከርካሪዎች ፣ የባቡር ሠራተኞች ፣ የአውሮፕላን ሠራተኞች እና በኖርዌይ ወደብ ወደ በመርከቦች የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ሰዓታት ውስጥ ከጉዞ ኳራንታይን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ።

በጠና የታመሙ ዘመዶችን ለመጎብኘት ፣ ወይም የቅርብ ዘመድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ ከጉዞ ኳራንታይን በልዩ ሁኔታ መካተት ይችላሉ። ይህ ተግባራዊ የሚሆነው የታመመውን ሰው በሚጎበኙበት ጊዜ ወይም በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ በሚሳተፉበት ጊዜ ብቻ ነው። ከዚህ ጊዜ ውጪ ኳራንታይን ተግባራዊ ይሆናል። ይህ ልዩ ሁኔታ ተግባራዊ የሚሆነው ድንበር ላይ ባደረጉት ምርመራ እና ጉብኝቱን ወይም የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሚካሄድበት ቀን ባደረጉት ምርመራ አሉታዊ የምርመራ ውጤት ካገኙ ብቻ ነው ። በነዚህ ሁኔታዎች ላይ በሚደረገው ምርመራ ክፍያውን እራስዎ መክፈል አለብዎት።

ተጨማሪ ያንብቡ (እንግሊዝኛ ብቻ)

በወላጆች እና በልጆች መካከል የሚደረግ የጋራ ግንኙነት

በወላጆች እና በልጆች መካከል በሚደረገው የጋራ ግንኙነት እና በተከፈለ ቋሚ የመኖሪያ ስፍራ ለልጆች የነበረው ልዩ ሁኔታ መርህ ተሽሯል።

ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች አሁን ከጉዞ ኳራንታይን ነፃ ናቸው ፣ ነገር ግን ኖርዌይ ከገቡ ከሶስት ቀናት በኋላ የPCR ወይም ፈጣን ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል።

ለአዋቂዎች (ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች) አሁን ዋናው ሕግ ሁሉም ሰው ኖርዌይ ከደረሰ ከሦስት ቀናት ጊዜ በኋላ ምርመራን በማድረግ ከጉዞ ኳራንታይን መውጣት ይችላል። ስለዚህም በልጆች እና ወላጆች በሚደረገው የአብሮነት ጊዜ በተመለከተ ከእንግዲህ የተለየ ልዩ መርህ የለም።

በኳራንታይን ጊዜ እንደበፊቱ ለከልጅዎ ጋር የአብሮነት ጊዜ ማሳለፍ ይችላሉ።

ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በብዙ ቋንቋዎች እዚህ ይገኛል (regjeringen.no)