ወደ ኖርዌይ መግቢያ – የኳራንቲን እና የምርመራ ህጎች

በዚህ ጊዜ ወደ ኖርዌይ መግባት የሚፈቀድላቸው የኖርዌይጃን ዜግነት ያላቸው እና ኖርዌይ በቋሚነት የሚኖሩ የውጪ ዜጎች ብቻ ናቸው። ከዚህ በታች በተገለጹት ሁኔታዎች የማይካተቱ የውጪ ዜጋ ተጉዋዦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሀሃገሪቱዋ ይባረራሉ።

የኖርዌይ መንግስት በኖርዌይ ሀገር ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በእጅጉ ጥብቅ አስፈላጊ ጉዞ ካልሆነ በስተቀር ከሀገር ውጪ ጉዞን እንዳያደርግ ይመክራል። ጥብቅ እና አስፈላጊ ካልሆነ ጉዞ ወደ ኖርዌይ የሚመለሱ ግለሰቦች ራስን ለይቶ በማቆያ ሆቴሎች ውስጥ ራሳቸውን ማግለል ይኖርባቸዋል፡፡

ወደ ኖርዌይ ለመጓዝ የተፈቀደላቸው እነዚህን ህጎች መከተላቸውን መቀጠል አለባቸው፡

 • ከመጓዝዎ በፊት የመግቢያ ምዝገባውን ቅፅ መሙላት አለብዎት
 • ከመድረስዎ በፊት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተደረገውን የ ኮቪድ-19 ኔጋቲቭ ምርመራ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለብዎት።
 • ወደ ኖርዌይ ሲደርሱ ምርመራ ማድረግ አለብዎት
 • በኖርዌይ ውስጥ ለ 10 ቀናት ራስዎን አግልለው ማቆየት አለብዎት

የኮቪድ-19 ደንቦችን መጣስ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ያስከትላል።

ብዙ ሰዎች በዚህ ጊዜ ወደ ኖርዌይ መጓዝ አይችሉም

ወደ ኖርዌይ የመግቢያ ገደቦች ከአውሮፓ ህብረት/ከአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ የመጡ ዜጎችን እና የኖርዲክ ዜጎችን ጨምሮ በሁሉም የውጭ ዜጎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል። ይህ የሚከተሉትን ያካትታል:

 1. ቱሪስቶች
 2. በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ያልተዘረዘሩ የቤተሰብ አባላት (የቅርብ የቤተሰብ አባላት ላይ ያለውን ክፍል ይመልከቱ)
 3. የወንድ ጓደኞች/የሴት ጓደኞች ወይምእጮኛዎች
 4. በኖርዌይ የሚሠሩ ወይም የሚማሩ እና ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ልዩ ምድቦች ውስጥ የማይካተቱ የአውሮፓ ህብረት/የአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ ዜጎች (የኖርዲክ ዜጎችን ጨምሮ)።
 5. የንግድ ተጓዦች
 6. የሸንገን ቪዛ የተሰጣቸው ፣ ግን ከዚህ በታች ካሉት ልዩ ሁኔታ ምድቦች ውስጥ የማይካተቱ የውጭ ዜጎች።
 7. በኖርዌይ ውስጥ የመዝናኛ ንብረት ያላቸው ፣ ግን እዚህ የማይኖሩ ሰዎች

ልዩ ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን በጣም የተለመዱት የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

 1. በኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ የውጪ ዜጎች የራሳቸው የሆነ ወይም የሚከራዩት ቤት ያላቸው።
 2. በኖርዌይ ላሉት ሰዎች ልዩ እንክብካቤ የማድረግ ሀላፊነቶች ያላቸው ወይም ኖርዌይ በሚኖሩ ሰዎች ልዩ እንክብካቤ ማግኘት፣ ወይም ሊሞቱ ያሉ ወይም በጠና የታመሙ የቅርብ የቤተሰብ አባላትን እንደመጠየቅ ያሉ ሌሎች የደህንነት ሁኔታዎች የመሳሰሉ የመግቢያ ልዩ ምክንያቶች ያላቸው የውጭ ዜጎች።
 3. ልጆቻቸውን የመጎብኘት ቀጠሮዎች የያዙ የውጭ ዜጎች።
 4. የቅርብ የትዳር ጓደኛ/የተመዘገበ አጋር/አብሮ-ነዋሪ ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ወይም የእንጀራ ልጆች ፣ ወላጆች ወይም የአሳዳጊ ልጆች ወይም የእንጀራ ልጆች ወላጆቻቸው ናቸው።
 5. ለውጭ ሚዲያ ተቋማት የተመደቡ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ሠራተኞች
 6. በኖርዌይ አየር ማረፊያዎች ትራንዚት የሚያደርጉ የውጭ ዜጎች (በዓለም አቀፍ የአየር ትራንዚትም ሆነ በሸንገን ውስጥ)
 7. የባህር መርከበኞች እና የአቪዬሽን ሠራተኞች
 8. በእቃዎች እና በተሳፋሪ ትራንስፖርት የተሰማሩ የውጭ ዜጎች
 9. ወሳኝ ማህበራዊ ተግባራትያለባቸው የውጭ ዜጎች - ከአሠሪ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው
 10. በኖርዌይ የጤና እንክብካቤ እና ማህበራዊ እንክብካቤ አገልግሎቶች ውስጥ የሚሠሩ የስዊድን እና የፊንላንድ የጤና እንክብካቤ ሠራተኞች
 11. አስፈላጊ የንግድ ሥራ ሠራተኞች። ሠራተኞች ወደ ኖርዌይ እንዲገቡ ከመፈቀዱ በፊት አሠሪዎች ከኖርዌይ ባለሥልጣናት ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው።
 12. ከድንበር ተሻግረው ወደ ኖርዌይ ትምህርት ለመከታተል በየቀኑ የሚጓዙ ልጆች።
 13. ወደ ኖርዌይ በየቀኑ ወደ ሥራ የሚጓዙ በስዊድን ወይም በፊንላንድ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች።

ሁሉንም የልዩ ሁኔታዎች ዝርዝር ለማግኘት የሚከተሉትን ይመልከቱ: lovdata.no (በእንግሊዝኛ ብቻ)

ከመግባት በፊት የሚደረግ ምዝገባ

ወደ ኖርዌይ ለመግባት የሚፈልጉ ሁሉ ከመግባታቸው በፊት የመግቢያ ምዝገባ ቅጽ መሙላት አለባቸው። በዲጂታል ሲመዘገቡ ሲደርሱ ለፖሊስ መቅረብ ያለበት ደረሰኝ ይደርስዎታል።

የምዝገባ ቅፁን ኖርዌይ ከመግባትዎ በፊት መሙላት አለብዎት ፣ ግን ከመግቢያው ከ 72 ሰዓታት በፊት አይደለም።

ዲጂታል የመግቢያ ምዝገባውን ይመልከቱ (entrynorway.no)

ስለኳራንታይን የትኞቹ ህጎች ለእርስዎ እንደሚተገበሩ እዚህ ይመልከቱ (Helsedirektoratet.no)

ምርመራ

የኮቪድ -19 ኔጋቲቭ ምርመራ ምስክር ወረቀት

ከመግቢያ ገደቦች ነፃ የሆኑ የውጪ ዜጎችና የኖርዌጂያን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሙሉ ወደ ኖርዌይ ድንበር ሲደርሱ የኮቪድ-19 ምርመራ መውሰዳቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማሳየት ይኖርባቸዋል። ማስረጃውም ግለሰቡ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን የሚያሳይ መሆን አለበት።  

 • ምርመራውኖርዌይ ከመድረስዎ በፊት ባሉት 24 ሰዓታት ውስጥ መከናወን አለበት።
 • PCR ወይም ፈጣን አንቲጂን ምርመራን ጨምሮ የተፈቀዱ የምርመራ ዘዴዎች።
 • የምስክር ወረቀቱ በኖርዌይኛ ፣ በስዊድንኛ ፣ በዳኒሽኛ ፣ በእንግሊዝኛ ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በጀርመንኛ መፃፍ አለበት።

በአውሮፕላን የሚመጡ ሰዎች የበበረራው የመጀመሪያ የበረራ ው ክፍል ከመነሻ ሰዓቱ በፊት ባሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራውን ሊያካሂዱ ይችላሉ።

የሚከተሉት ሰዎች የኔጋቲቭ ምርመራ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አያስፈልጋቸውም፡

 1. የኳራንቲን ግዴታ ከሌላቸው ሀገሮች ወይም ክልሎች የመጡ ሰዎች
 2. ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች
 3. ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ኮሮና ይዟቸው እንደነበር የማስረጃ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ግለሰቦች። ሰነዱም የኮሮና ምርመራን ማድረግ የሚችል ፍቃድ ካለው ላቦራቶሪ የተሰጠ መሆን አለብት
 4. ኅብረተሰቡ ውስጥ ጥብቅና ወሳኝ ተግባር ያላቸው ወይም የሕዝቡን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት አስፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎች። ሆኖም ግን በዚህ የሚጠቃለሉት ወደ ኖርዌይ አለመግባታቸው የሰው ጤና እና ህይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ከታሰበ ነው።
 5. በትራንዚት ላይ ያሉ የውጭ ዜጎች
 6. ለሥራ ወይም ለትምህርት ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ በመደበኛነት ወደ ኖርዌይ የሚጓዙ እና ከሰባት ቀናት በላይ ከኖርዌይ ውጭ የቆዩ የውጭ ዜጎች። ከስዊድን እና ከፊንላንድ የሚመጡ የጤና እንክብካቤ ሠራተኞች ለምስክር ወረቀቶች የተለዩ መስፈርቶች አሏቸው። ለሠራተኞች እና ለተጓዦች የመግቢያ ኳራንቲን ክፍልን ይመልከቱ።
 7. ጥገኝነት ፈላጊዎች እና የኮታ ስደተኞች።
 8. በኖርዌይ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ዜጎች በቤተሰብ ፍልሰት ደንብ መሠረት።
 9. በኖርዌይ ዕውቅና የተሰጣቸው የዲፕሎማሲ እና የቆንስላ ሠራተኞች
 10. በእቃዎች እና በተሳፋሪ ትራንስፖርት ላይ የተሰማሩ ወይም ወደ እንደዚህ ዓይነት ተልእኮ በመሄድ ላይ ወይም በመመለስ ላይ የውጭ ዜጎች።
 11. ወደ ተልእኮ የሚሄዱ ወይም ከተልእኮ የሚመለሱ አብራሪዎች ወይም የባህር መርከበኞች።
 12. በምትኩ በየ 7 ቀኑ የኮቪድ -19 ምርመራን የሚያካሂዱ እና ይህንን ማስመዝገብ የሚችሉ ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ የሚመጡ ተጓዦች።
 13. የስቫልባርድ ቋሚ ነዋሪዎች
 14. በጉዞ ላይ ያሉ የስዊድን ወይም የፊንላንድ ፖሊሶች እና ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ አገልግሎት ሊሰጡ የመጡ የጉምሩክ ሠራተኞች።

በትራንዚት ጉዞ ላይ ያሉ የስዊድን ወይም የፊንላንድ ፖሊሶች እና ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ አገልግሎት ሊሰጡ የሚመጡ የጉምሩክ ሰራተኞች።

ወደ ኖርዌይ ሲመለሱ ያሉ የምርመራ መስፈርቶች

ወደ ኖርዌይ ጉዞ ከማድረጎ በፊት ከቫይረሱ ነፃ መሆኖን የሚያሳይ የምርመራ ምስክር ወረቀት ከማሳየት በተጨማሪ ወደ ኖርዌይ እንደደረሱ ወዲያውኑ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ አለብዎት። በድንበሩ ላይ የምርመራ ጣቢያዎች አሉ፡፡ የምርመራ ውጤንቶ እስኪያገኙ ድረስ በቦታው ላይ የመጠበቅ ግዴታ አለብዎት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግማሽ ሰዓት ይወስዳል። የምርመራው ውጤት ቫይረሱ በሰውነቶ ውስጥ እንዳለ በሚያሳይ ጊዜ ኖርዌይ ከደረሱ ከአንድ ቀን በኋላ የPCR  ምርመራ መውሰድ ይኖርብዎታል፡፡

ዕድሜያቸው ከ  ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትም ምርመራ ማድረግ አለባቸው ሆኖም ግን ምርመራውን ለማድረግ አስቸጋሪ ከሆነ ለምሳሌ ልጁ እልመረመርም ብሎ ካስቸገረ ምርመራው መቅረት አለበት።

በቂ ምክንያት የሌላቸው ሰዎች፣ ላለመመርመር ፈቃደኛ ያልሆኑ ወይም በፈቃደኝነት አገር ለቀው የሚጓዙ ግለሰቦችች ቅጣት ይቀጣሉ።

የኳራንቲን ጊዜውን በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ የማያሳልፍ ግለሰብ ኖርዌይ ከገባ ከሰባት ቀናት በኋላም የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ አለበት።

ወደ ስቫልባርድ ጉዞ የሚያደርጉ አብዛኛዎቹ ሰዎች ስቫልባርድ ከመድረሳቸው በፊት በ 24 ሰዓታት ውስጥ በኖርዌይ የተወሰደ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም የምስክር ወረቀቱ ቫይረሱ በግለሰቡ ሰውነት ውስጥ እንደሌለ ማረጋገጥ መቻል አለበት።

በኖርዌይ ድንበር ላይ ከሚደረገው የምርመራ መስፈርቶች ነፃ የሆኑ ግለሰቦች፡

 1. በሥራ ሰዓት እና ከስራ ሰዓት ውጪ ከኳራታይን መርህ ነፃ የሆኑ ግለሰቦች ፡፡ እነዚህ ማን እንደሆኑ ስለ ኳራታይን በተፃፈው አንቀጽ ይመልከቱ ፡፡
 2. ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ በመደበኛነት የሚጓዙ ፣ ከመግቢያ ገደቦች ነፃ የሆኑ እና የእራሳቸውን የምርመራ ህግ የሚከተሉ ሰዎች።
 3. የረጅም ጭነት መኪና አሽከርካሪ ሙያተኛዎች እና በጭነት ባቡሮች የማይሠሩ የባቡር ሠራተኞች እንዲሁም በጭነት ባቡሮች ላይ የሚሠሩ የተወሰኑ የባቡር ቡድን ሠራተኞች።
 4. ምርመራውን ለማካሄድ ተግባራዊ ካልሆነ እና ወሳኝ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ወይም የህዝቡን መሠረታዊ ፍላጎቶች ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ ግለሰቦች ከሆኑ።
 5. ዲፕሎማቶች።
 6. በኖርዌይ ሥራቸውን የሚጀምሩ እና ከአውሮፕላኑም ሆነ ከባቡር ሳይወጡ ወደ ውጭ የሚጓዙ የአውሮፕላን ሠራተኞች እና የባቡር ሠራተኞች በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ ከኳራታይን ነፃ ናቸው፡፡
 7. ለዓለም አቀፍ ውይይት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ በኖርዌይ ባለሥልጣናት የተጋበዙ የውጭ ዜጎች እና ወደ ኖርዌይ የሚመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የሆኑ የውጭ ዜጎች፡፡

ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ በኖርዌይ በኩል የሚጓዙ የፖሊስ እና የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ ለስራ ወደ ኖርዌይ የመጡ የጉምሩክ ሰራተኞች።

ኳራንቲን

ኖርዲክ ክልል ወይም አውሮፓ ውስጥ ከተወሰኑ አካባቢዎች ከሚመጡ እና ዝቅተኛ የበሽታ ስርጭት ደረጃ (ቢጫ ክልሎች ወይም ሀገሮች) ከሚመጡት በስተቀር ከሌላ ሀገር ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ሁሉም ሰዎች ለ 10 ቀናት ያህል ለብቻ መሆን አለባቸው።

የቀይ እና ቢጫ ሀገሮች/ክልሎች ካርታ በአውሮፓ (በእንግሊዝኛ ብቻ)

በኮቪድ -19 ተይዘው የዳኑ ሰዎች ከኳራንቲን ህጎች ነፃ አይደሉም። ወደ ኖርዌይ ከገቡ በኋላ ወዲያውኑ ወደ የኳራንቲን ጣቢያ መጓዝ ይኖርብዎታል። 

ከጉዞ ሲመለሱ የመግቢያ ኳራንቲን ደንቦች

 • የመግቢያ ኳራንቲን ጊዜን በኳራንቲን ሆቴል ማሳለፍ ወይም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የኳራንቲን ሆቴል መስፈርት ነጻ ከሆኑ ደግሞ በሌላ ተስማሚ መጠለያ ማሳለፍ አለብዎት።
 • ከቤተሰብዎ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር የቅርብ ርቀት ግንኙነት ማድረግን ማስወገድ የሚችሉ ከሆነ ብቻ የኳራንቲን ቦታዎን መልቀቅ ይችላሉ።
 • ሌሎች የሚገኙበትን የሥራ ቦታ ወይም ትምህርት ቤት ወይም የቀን እንክብካቤ ተቋም መጎብኘት አይችሉም።
 • ወደ ኖርዌይ መግባት እና ከኖርዌይ መውጣት ጋር ተያይዞ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ ወደብ ወይም ተመሳሳይ ቦታ ከመጓዝ/መውጣት በስተቀር የህዝብ ማመላለሻን መጠቀም አይችሉም። ከ 12 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው የፊት ጭምብል መልበስ አለበት።
 • በኳራንቲኑ ወቅት ከአንድ ሰው ጋር የሚኖሩ ከሆነ የተለዩ መኝታ ቤቶች እና መታጠቢያ ቤቶች ሊኖሩዎት እና ሁለት ሜትር ርቀት ላይ መቆየት ይኖርብዎታል። ይህ የማይቻል ከሆነ ፣ አብረዋቸው የሚኖሯቸው ሰዎችም ኳራንቲን ማድረግ አለባቸው ፣ ወይም እርስዎ በማዘጋጃ ቤቱ በሚመከረው ሆቴል ወይም ሌላ ማረፊያ ተለይተው መቆየት አለብዎት።
 • እንዲሁም ወደ ቤትዎ ከተመለሱ ከሰባት ቀናት በኋላ በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ ሰዎች መመርመር አለባቸው (ለእርስዎ የግድ ሲሆን ለቤተሰብዎ ግን የሚመከር)።
 • በኳራንቲን ጊዜዎ የኮቪድ-19 ምልክቶችን ካሳዩ እራስዎን ማግለል እና ለምርመራ የአከባቢውን የጤና አገልግሎቶች ማነጋገር አለብዎት። የስልክ ቁጥር 116117

ያጠረ የኳራንታይን ጊዜ

ወደ ኖርዌይ ከገቡ ከሰባት ቀናት በኋላ የተወሰደው የኮሮና ቫይረስ የምርመራው ውጤት ኔጌቲቭ ከሆነ የጉዞ ኳራንታይኖን ማሳጠር ይችላሉ፡፡ በኳራንቲን ሆቴሎች ውስጥ ለማይቆዩ ግለሰቦች ሁሉ ይህ ምርመራ ግዴታ ነው፡፡ የኮሮና ምርመራው ውጤት እስከሚመጣና ቫይረሱ በሰውነቶ ውስጥ እንደሌለ እስከሚያሳይ ድረስ የኳራንታይን ግዴታው ተግባራዊ ይሆናል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን ምርመራ ለማድረግ ኮሚዩናውን ወይም ምርመራውን የሚያካሄደውን ማዕከልን ያነጋግሩ፡፡

የመግቢያ ኳራንቲን የት መደረግ አለበት?

ዋናው ደንብ ኖርዌይ ውስጥ ቋሚ መኖሪያ ያላቸውን ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ውስጥ መቆየት ይኖርበታል። ስለ ኳራንቲን ሆቴሎች ተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ክፍል ውስጥ ያንብቡ።

የቅርብ ዘመድ (ባለትዳሮች ፣ አብሮ ኗሪዎች እና ልጆቻቸው) በአገራቸው አብረው የሚኖሩ እና አብረው ወደ ኖርዌይ የሚጓዙ በተመሳሳይ የመጠለያ የመግቢያ የኳራንቲን አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ።

የጉዞ ካራንቲንዎ ሊከናወን የሚችለው፡

 • ድንበር በሚያቋርጡበት ቦታ በሚገኘው የኳራንቲን ሆቴል ውስጥ።
 • በኖርዌይ ውስጥ በቋሚነት መኖርያ ቤት ውስጥ ፣ የእርስዎም ሆነ የኪራይ። ይህ እንደ ካምፕ ቫኖች ፣ ጀልባዎች ወይም ተመሳሳይ ላሉት ተንቀሳቃሽ ማረፊያዎች አይመለከትም። ሲገቡ የባለቤትነት ወይም የኪራይ ሁኔታን ማስመዝገብ መቻል አለብዎት ፣ እናም የተከራይና አከራይ ውል ቢያንስ ለስድስት ወር የሚሠራ መሆን አለበት። ከርስዎ ጋር የሚኖሩት የተናጥል የመኝታ ክፍሎች እና የመታጠቢያ ክፍሎች ከሌሉ በስተቀር እንዲሁ እራሳቸውን እንዲለዩ ይበረታታሉ።
 • በተለየ ተስማሚ መጠለያ ውስጥ ፣ በዚህ ቦታ እንዲኖሩ የሚያስፈልጉዎ ጠንካራ ደህንነት ጉዳዮች መኖራቸውን ወደ ኖርዌይ ሲገቡ በሰነድ ማቅረብ ከቻሉ። እንዲሁም ቦታው ለለይቶ ማቆያ ማረፊያ ተስማሚ መሆኑን በሰነድ ማረጋገጥ መቻል አለብዎት። ከዚህ ዝርዝር በታች ላሉት ተስማሚ ማረፊያዎች ማብራሪያ ይመልከቱ።
 • በተጋቡበት ሰው ወይም ልጅ ከወለዱለት ሰው ቤት ውስጥ። ሲገቡ እንደተጋቡ ወይም የጋራ ልጅ እንደወለዱ በሰነድ ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለብዎት። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችዎም እዚህ በኳራንቲን ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ።
 • በአሠሪዎ በተረጋገጡ ተስማሚ ማረፊያዎች። ሠራተኛው ወደ ኖርዌይ ከመግባቱ በፊት አሠሪው በኖርዌይ የሠራተኛ ቁጥጥር ባለሥልጣን መኖሪያ ቤቶቹን ያፀደቀ መሆን አለበት። ሲገቡ ይህንን ማረጋገጫ በሰነድ ማስመዝገብ መቻል አለብዎት።

ተስማሚ ማረፊያዎች፡ ከሌሎች ጋር የቅርብ ርቀት ግንኙነትን ማስወገድ መቻል አለበት። ማረፊያዎቹ በቴሌቪዥን እና በይነመረብ ፣ የእራሱ መታጠቢያ ቤት እና የእራሱ ማብሰያ ክፍል ወይም ምግብ ቤት ያላቸው የአንድ ሰው ክፍል ሊኖራቸው ይገባል።

የመግቢያ ምዝገባ አስገዳጅ ቅጽ ውስጥ ፣ መኖሪያው የኳራንቲን መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማካተት አለብዎት።

ወደ ኖርዌይ የሚገቡ ተጓዦች መቆጣጠሪያ ብሔራዊ ማዕከል

በኳራንቲኑ ወቅት ወደ ኖርዌይ የሚጓዙ መንገደኞች የኖርዌይ ተጓዦች መቆጣጠሪያ ብሔራዊ ማዕከል በአጭር የጽሑፍ መልዕክት እና በስልክ ያገኛቸዋል።

የመቆጣጠሪያ ማዕከሉ ከእርስዎ ጋር መገናኘት ካልቻለ ይህ ወደ ማዘጋጃ ቤቱ ዶክተር ወይም ለሠራተኛ ቁጥጥር ባለሥልጣን ሊተላለፍ ይችላል። የመቆጣጠሪያ ማዕከሉ ከመግቢያ ምዝገባው ስለእርስዎ መረጃ ይቀበላል።

በስልክ ቁጥር 2189xxxx ከተደወለልዎት ስልክ ማንሳቱ አስፈላጊ ነው።

ከዚህ በታች የተጠቀሱት ሰዎች በሥራ ሰዓትም ሆነ በመዝናኛ ጊዜ ከጉዞ ኳራንታይን ነፃ ናቸው

 1. ዃራንታይ ግዴታ ከሆነበት ሀገር ጉዞ አድርገው ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ግለሰቦች የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ካልተጠቀሙ ፣ በቦታው ሳያድሩ እና አብረዋቸው ከሚኖሩት ሰዎች በስተቀ ከሌሎች ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ካልነበራቸው።
 2. በስዊድን ወይም ፊንላንድ ቋሚ ህንፃ፣ ጀልባን ወይም ተንቀሳቃሽ ካምፒንግ ቮግን ወይም የመሳሰሉት ላይ አስፈላጊ ጥገና እና ቁጥጥር አድርገው ወደ ኖርዌይ የሚገቡ ተጓዦች። ሆኖም ግን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ካልተጠቀሙ ፣ በቦታው ሳያድሩ እና አብረዋቸው ከሚኖሩት ሰዎች በስተቀ ከሌሎች ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ካልነበራቸው ነው።
 3. ከኖርዌይ ጀልባ ላይ ተሳፍረው እና ወደ ኖርዌይ እስኪመለሱ ድረስ በጀልባው ላይ ብቻ ቆይታ የሚያደርጉ ግለሰቦች፡፡ በውጪ ወደብ ባህር ዳርቻ ላይ የነበሩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ወይም ሠራተኞች መሳፈር አይችሉም። ሆኖም ግን ይህ ዕቃዎችን በማጓጓዝ የሚሰሩ ግለሰቦች ከሆኑ እና ከተሳፋሪዎችና ሠራተኞች ጋር የቅርብ ግንኙነትን ካላደረጉ አያካትትም።
 4. በኖርዌይ ሥራቸውን የሚጀምሩ የአውሮፕላንና የባቡር ሰራተኞች ከአውሮፕላኑ ወይም ከባቡሩን ሳይወጡ ወደ ውጭ አገር የሚጓዙ ሠራተኞች፡፡ አውሮፕላኑን ወይም ባቡሩን ለቀው ከሄዱ ወደ ኖርዌይ እንደደረሱ (ለአውሮፕላን ሰራተኞች) ወይም በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት(ለባቡር ሠራተኞች) መመርመር እና ከዚያም በየሰባቱ ቀናት ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡

የመግቢያ የኳራንቲን ለሠራተኞች እና ለተጓዦች

የውጭ ሠራተኞች በአጠቃላይ በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ ኳራንቲን ማድረግ አለባቸው። የኳራንቲን ግዴታ ካለበት አገር ወደ ኖርዌይ የሚመጣ ማንኛውም ሰው፡ 

 • ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለ 10 ቀናት ሙሉ ለብቻ መሆን አለባቸው
 • ከላይ ባለው ክፍል እንደተገለጸው ኔጋቲቭ የኮሮናቫይረስ ምርመራን ተከትሎ የጉዞ ኳራንቲንን ማሳጠር ይችላል

ልዩ ሁኔታዎች በሥራ ሰዓታት የብሔራዊ ድንበርን አዘውትረው ለሚሻገሩ ሰዎች

 • በሆስፒታሎች ወይም በኮሚዩና ውስጥ በጤና አገልግሎት ወሳኝ ኃላፊነት ያላቸው እና ሙሉ በሙሉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰዱ የጤና ባለሙያዎች ወደ ኖርዌይ ሲገቡ የምርመራ ውጤታቸው ቫይረሱ በደማቸ ውስጥ እንደሌለ ካሳየ በሥራ ሰዓት ከኳራንቲን ነፃ ናቸው።
 • የረጅም ርቀት ትራንስፖርት ሙያተኛ አሽከርካሪዎች ፣ የባቡር ሠራተኞች ፣ የአየር መንገድ ሠራተኞች እና በኖርዌይ ወደብ ላይ ባሉ መርከቦች ለሥራ የሚሄዱ ሠራተኞች በሥራ ሰዓታት ከጉዞ ኳራንቲን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ። ምን ዓይነት ህጎች ተግባራዊ እንደሚሆኑ ለማወቅ እነዚህ ግለሰቦች ቀጣሪዎቻቸውን መጠየቅ ይኖርባቸዋል።
 • ለስራ የሚመጡ የስዊድን ወይም የፊንላንድ ፖሊሶች እና አንዳንድ ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ አገልግሎት ሊሰጡ የሚመጡ የጉምሩክ ሰራተኞች በስራ ሰዓት ላይ ከኳራንቲን ህግ ነፃ ናቸው።
 •  
 • የ 15 ቀን ጊዜ ቆይታ በላይ ከአንድ ጊዜ በላይ ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ የኖርዌይ ድንበርን የሚሻገሩ ተጓዦች ፣ ከሥራ ሰዓት ኳራንቲን ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እንደሚከተለው እራሳቸውን የመረመሩ ከሆነ:
 1. በየ 7 ቀን አንድ ጊዜ

ወይም

 1. ወደ ኖርዌይ ሲገቡ በመጀመሪያው ቀን ፣ ከዚያ በኋላ በየ ሰባተኛው ቀን ፣ ኖርዌይ ውስጥ ከተመረመሩ ከሰባት ሙሉ ቀናት በላይ ማለት ነው

ወይም

 1. ለመጨረሻው የጊዜ የኮቪድ-19 ምርመራ በስዊድን ወይም በፊንላንድ ውስጥ ከተወሰደ በሰባት ሙሉ ቀናት ጊዜ ውስጥ (ለቀን ተጓዦችን ብቻ የሚመለከት) 

ወደ ኖርዌይ ከመምጣትዎ በፊት ባሉት 10 ሙሉ ቀናት ውስጥ ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ ውጭ ወደ ሌላ አገር ሄደው ከሆነ ወይም በተመሳሳይ ጊዜ በስዊድን ወይም በፊንላንድ የጤና እና እንክብካቤ አገልግሎቶች ውስጥ የሚሠሩ ከሆነ ነፃ ሊሆኑ አይችሉም።

ተጨማሪ ያንብቡ (እንግሊዝኛ ብቻ)

ልዩ ሁኔታዎች

በአንዳንድ ሁኔታዎች ከመግቢያ የኳራንቲን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ፡

 • በጠና የታመሙ የቅርብ የቤተሰብ አባላትን ለመጎብኘት ወይም የቅርብ የቤተሰብ አባላት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ። የኳራንቲን ነፃ መሆን የሚመለከተው የታመመውን ሰው በሚጎበኙበት ወይም በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በሚሳተፉበት ጊዜ ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ኳራንቲን ይተገበራል። ነፃ መሆን ተፈጻሚ የሚሆነው ድንበሩ ላይ ኔጋቲቭ ምርመራ ካደረጉ እና ጉብኝቱ ወይም የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሚከናወንበት ቀን ብቻ ነው። በዚህ ጊዜ ለምርመራው እራስዎ መክፈል አለብዎት።
 • በሕፃናት ሕግ ወይም በሕፃናት ደህንነት ሕግ መሠረት ልጆችዎን የመጎብኘት ስምምነት ካልዎት ይህን በሚተገብሩበት ሰዓታ ክኳራንቲን ህግ ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ፡
 • ኖርዌይ ውስጥ ከሚኖሩ ልጆች ጋር ለመሆን ከውጭ አገር የሚመጡ ከሆነ ከኳራንቲን ነፃ አይሆኑም ፣ ነገር ግን በኳራንቲኑ ወቅት ከልጆችዎ ጋር ሊሆኑ ይችላሉ።
 • ውጭ አገር ካሉ ልጆችዎ ጋር ለመኖር ውጭ አገር የነበሩ ከሆነ ፣ ኖርዌይ ከደረሱ ከ 3 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለተወሰደው ምርመራ (PCR) ኔጋቲቭ ከሆኑ በሥራ ሰዓታት ከመግቢያ ኳራንቲን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ። በኖርዌይ ውስጥ ሥራ ከሌለዎት ከልጆችዎ ጋር ለመሆን በሚመጡበት ጊዜ በሥራ ሰዓት ከኳራንቲን ነፃ አይሆኑም።
 • ከወላጆቻቸው ጋር ከሆኑ በኋላ ከውጭ አገር የሚመጡ ልጆች ኖርዌይ ከገቡ ከ 3 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለ (PCR) ምርመራ ኔጋቲቭ ከሆኑ ፣ በትምህርት ሰዓት ውስጥ ከኳራንቲን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከኳራንቲን ነፃ ከሆኑ እና የኮቪድ-19 ምልክቶችን ካሳዩ ወይም በዶክተር ተመርምረው የኮቪድ-19 በሽታ እንዳለብዎት ከተጠረጠረ አሁንም ኳራንቲን ማድረግ አለብዎት።

የኳራንቲን ሆቴሎች

ወደ ኖርዌይ ሲገቡ ራስን ለማግለያ በተዘጋጁ ሆቴሎች እራሶን አግልለው ማቆየት አለቦት። ወደ ኖርዌይ ሲገቡ ከዚህ በላይ ከተጠቀስው ሕግ ነፃ የሚያደርጎት የማስረጃ ሰነድ ካልያዙ መርሁን ተግባራዊ ማድራግ ይኖርቦታል።ስለኳራንቲን ሆቴሎች መረጃ በኖርዌይ ድንበር እና መድረሻ ቦታዎች ከፖሊስ ሊያገኙ ይችላሉ።

የኖርዌይ መንግስት በኖርዌይ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በእጅጉ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ጉዞ ማድረጉን እንዲያስቀር ይመክራል።

ጥብቅ አስፈላጊ ጉዞ ተብለው የሚታሰቡት የስራ ጉዞዎች ወይም አስገዳጅ ለሆኑና የደህንነት ጉዳይ ጉዞዎች ናቸው። ጠንካራ የደህንነት ጉዳዮች ተብለው የሚመደቡት ለምሳሌ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በውጭ የሚኖሩ ከሆነ፣ በጠና የታመመ ወይም የሚሞት የቅርብ ዘመድ ለመጎብኘት፣ ለሚቀርብዎ ሰው የቀብር ስነ ስርዓት ወይም በውጭ አገር አስፈላጊ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈለጎት ከሆነ ነው፡፡

በጠና ያልታመመ የትዳር ጓደኛን፣ የፍቅር ጓደኛን ወይም ሌሎች የቅርብ ዘመዶችን መጎብኘት ጠንካራ የደህንነት ጉዳይ አይደለም፡፡

ጉዞው ጥብቅና አስፈላጊ እንደነበረ ማስረጃ ማቅረብ አለብዎት፡፡ በተጨማሪም ራስዎን የማግለያ ቤት እንዳሎት ማስረጃ ማቅረብ አለቦት። ቤቱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ርቀቶን መጠበቅ የሚችሉበት፣ የግል ክ ፍል፣ የግል መታጠቢያ ያለው እና የግል ኩሽና ወይም ምግብ የሚያቀርብሎት አገልግሎት ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ማስረጃ ማቅረብ ካልቻሉ በኳራንታይን ሆቴል መቆየት አለብዎት፡፡ የሆቴሉን ወጪ እራስዎ መክፈል ይኖርቦታል፡፡ ሆቴሉ ውስጥ ቢያንስ ለሰባት ቀናት መቆት አለብዎት፡፡ በሰባተኛው ቀን አዲስ የኮሮና ምርመራ ማድረግ ይችላሉ፡፡ የምርመራው ውጤት ቫይረሱ በደሞ ውስጥ እንደሌለ ካሳየ ቀሪውን የኳራንቲን ጊዜ በራስዎ ቤትተ ውይም ተስማሚ በሆነ የመኖሪያ ቦታ ውስጥ ማከናውን ይችላሉ ፡፡

ሆቴሉ ውስጥ በሚያርፉበት ጊዜ ወጪዎቹ በእራስዎ ይሸፈናሉ፡፡ በዚያም ቢያንስ ለሰባት ቀናት መቆየት አለብዎት፡፡ በሰባተኛው ቀን አዲስ ምርመራ ማድረግ ይችላሉ፡፡ የምርመራው ውጤት ቫይረሱ እንደሌለቦት ካሳየ ኳራንታይኑን ማቆም ይችላሉ፡፡

ምርመራ ማድረግ የሚችሉት በሰባተኛው ቀን ሲሆን ይህም ኮሚውነው አቅም ካለው ብቻ ነው፡፡ በጠንካራ የደህንነት ጉዳዮች ምክንያት የተጓዙበት ሰነድ ማለት ለምሳሌ፣ የወላጅና-ልጅ ጉብኝት ወይም የሐኪም መግለጫ ሲኖሮት ነው፡፡

ወደ ኖርዌይ ብቻቸውን የሚገቡ እና ከኳራንቲን ነፃ ያልሆኑ ታዳጊዎች በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ ከሚንከባከባቸው ሰው ጋር የመቆየት እድል አላቸው።

ወጪዎች

ለካራንቲን ሆቴል የሚከፈለው ክፍያ ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ የግል ግለሰቦችና ለአሠሪዎች በቀን 500 ክሮነር ነው። ዕድሜያቸው ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ ከ ወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር ክፍሎች ውስጥ የሚቆዩ ልጆች በነፃ ይቆያሉ። ከ 10 እስከ 18 ዓመት ለሆኑ ሕጻናት የሚከፈል ክፍያ በቀን 250 የኖርዌይ ክሮነር ነው። በኳራንቲን ሆቴል የክፍያ መጋራት ክፍያ ሲደርሱ ወይም ከመንሳት አስቀድሞ እንደተለመደው ይከፈላል።

ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ ይሰጣል።

ከዚህ በታች የሚከተሉት በኳራንቲን ሆቴል መቆየት አያስፈልጋቸውም:

 1. ወደ ኖርዌይ ሲገቡ ኖርዌይ በቋሚነት ነዋሪ መሆናቸውን፣ ጉዞው አስፈላጊ እንደነበረና ፣ በቤታቸው ውስጥ ወይም በሌላ ተስማሚ የመኖሪያ ስፍራ ራሳቸውን የሚያገሉ መሆናቸው የሚያሳይ ማስረጃ ያላቸው ግለሰቦቸ። የመኖሪያ ማስረጃ ሰነድ ተብሎ የሚታሰበው ለምሳሌ ሀገሪቷ ውስጥ በነዋሪነት ህጋዊ ተመዝጋቢ ከሆኑ፣ ወይም በታክስ አስተዳደር የተመዘገበ መኖሪያ ቤት አድራሻ ካሎት ወይም ቢያንስ ለስድስት ወር የሚቆይ የቤት ኪራይ ውል ካሎት ነው። ይህ ልዩ ሁኔታ ባለትዳር ለሆኑ ወይም ነዋሪነቱን በኖርዌይ ካደረገ ግለሰብ ጋር የጋራ ልጆች ላሏቸው እና ለአቅመ አዳም/ ሆዋን ያልደረሱ ልጆቻቸውንም አብረው ወደ ኖርዌይ ከተጓዙ ይመለከታል፡፡ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሰዎች የኳራንቲን ጊዜያቸውን በትዳር አጋራቸው ቤት ወይም በሌላኛው ወላጅ ቤት ውስጥ ማከናወን ይችላሉ።
 2. አሠሪዎቻቸው ወይም ደንበኛቸው ለአንድ ሰው የሚሆን የመኖሪያ ክፍል ያላቸውን ተስማሚ ማረፊያዎች የሚያቀርቡላቸው የንግድ ተጓዦች። እርስዎእየሠሩ ወይም በፕሮጀክት ላይ እየሠሩ መሆንዎን እና አሠሪው ወይም ደንበኛው ማረፊያዎችን ያፀደቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ሊኖርዎት ይገባል። ማረፊያዎቹ ከሌሎች ጋር የቅርብ ርቀት ግንኙነትን ለማስወገድ የሚያስችሉ እና ቴሌቪዥን እንዲሁም የእራሱ መታጠቢያ ፣ የእራሱ ማብሰያ ክፍል ወይም ምግብ ቤት ያለው ባለአንድ ሰው ክፍል ያላቸው መሆን አለባቸው። ሰነዱ ለምሳሌ የሥራ ቅጥር ወይም የፕሮጀክት ውል ሊሆን ይችላል።  ይህም ዬት እንደሚኖሩ እንዲሁም የአሠሪዎ ወይም የደንበኛዎ ስም ፣ አድራሻ እና የስልክ ቁጥር ማካተት አለበት።
 3. ጠንካራ የደህንነት ጉዳይ እንደነበራቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ለምሳሌ ልዩ ክትትል የሚፈልግ ህመም ያላቸው እና የኳራንቲን ሆቴሉ ይህን አገልግሎት ሊያቀርብላቸው የማይችሉ። በተጨማሪም ወደ ሀገር ሲገቡ የመኖሪያ ቦታው ተስማሚ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 4. ጥገኝነት የሚያመለክቱ ወይም የዝውውር ስደተኛ የሆኑ፡፡
 5. ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አንዳንድ የሙያ ሠራተኞች ሥራ ለመስራት መምጣታቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እንዲሁም ከኳራንቲን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልነት ነፃ መሆናቸው በማስረጃ ማሳየት መቻል አለባቸው። 
 6. በመከላከያ ሚኒስቴር ለተፈቀደ ስልጠና ፣ ልምምዶች ወይም ሥራዎች ወደ ኖርዌይ የሚመጡ የውጭ ወታደራዊ ሀይሎች።
 7. በትራንዚት ጉዞ ላይ ያሉ የስዊድን ወይም የፊንላንድ ፖሊሶች እና ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ አገልግሎት ሊሰጡ የሚመጡ የጉምሩክ ሰራተኞች።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በመኖሪያ ቤቶ ውስጥ ወይም ሌላ ተስማሚ በሆነ ቦታ ራሶን አግልለው እንዲቆዩ ያስገድዳሉ።

ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በብዙ ቋንቋዎች እዚህ ይገኛል (regjeringen.no)

----

እዚህ ተጨማሪ ያንብቡ፡ helsenorge.no/corona-xx

ይዘቱ በኖርዌይ የጤና ዳይሬክቶሬት የተበረከተ ነው / Content provided by the Norwegian Directorate of Health