ህጋዊ መኖሪያ የሌላቸው ሰዎችን በተመለከት ስለ COVID-19 መረጃ

በኖርዌይ ወስጥ ማንኛውም ሰው COVID-19 ካለበት ነጻ የCOVID-19 ምርመራ እና የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት አለው

የCOVID-19 ምልክቶች ሳል፣ ትኩሳት፣ ትንፋሽ ማጣት፣ እና የማሽተት እና የመቅመስ ችሎታ ማጣትን ያጠቃልላሉ። የCOVID-19 ምልክቶችን ካሳዩ ወይም እንደተያዙ የሚያስቡ ከሆነ የጤና እንክብካቤ አገልግሎትን ያግኙ። በከተማዎ ውስጥ የጤና እንክብካቤ ወይም ከስራ ሰዓት ውጪ የሚሰሩ የአደጋ ጊዜ የህክምና አገልግሎትን በስልክ ማግኘት ይችላሉ፡ 116117።

በኦስሎ ወይም በርገን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ በህጋዊ ላልሆኑ ስደተኞች የጤና ማዕከል አማካኝነት በምርመራ እና በጤና እንክብካቤ ላይ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

የCOVID-19 ምርመራ ነጻ ነው።

የጤና እንክብካቤ አገልግሎትን ሲገናኙ፣ ፓስፖርት ወይም ሌላ መታወቂያ ማሳየት አይጠበቅብዎትም።

አስተርጓሚ ከፈለጉ ሊያሳውቋቸው ይገባል። በቋንቋዎ አስተርጓሚ የማግኘት መብት አልዎት። የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች አስተርጓሚ መቅጠር ይችላሉ። ይህ ለእርስዎ ነጻ ነው። አስተርጓሚውም የምስጢራዊነት ግዴታ አለበት። 

ምርመራውም የሚያካሄዱ የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች ፈጣን ምርመራ ወይም መደበኛ ምርመራ ለማካሄድ መምረጥ ይችላሉ። ፈጣን ምርመራ ከወሰዱ፣ ውጤቱን በ20 ደቂቃ ውስጥ ያገኛሉ። መደበኛ ምርመራ ከወሰዱ፣ ውጤቱን ከ1-4 ቀናት ውስጥ ያገኛሉ።

የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች የምስጢራዊነት ግዴታ አለባቸው። ይህ ማለት ስለ እርስዎ እና ስለ ጤንነትዎ ለማንም መረጃን አያጋሩም ማለት ነው።

COVID-19 ካለብዎት፣ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት። በሚቆዩበት ቦታ ለ10 ቀናት ወይም ትኩሳትዎ እስኪጠፋ ድረስ ነጻ መስተንግዶ ይቀርብልዎታል። ምግብ እና መጠጥ ይሰጥዎታል። እለይቶ ማቆያ ውስጥ እያሉ፣ ጠያቂዎች ሊኖርዎት አይችልም። ሌላ ሰውን መጠየቅ ወይም ወደ ውጪ መውጣትም አይችሉም።

COVID-19 ካለበት ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበረዎ፣ ለ10 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አለብዎት። በለይቶ ማቆያ ወቅት በሚቆዩበት ቦታ ነጻ መስተንግዶ እና ነጻ ምርመራ ይቀርብልዎታል። ምግብ እና መጠጥ ይሰጥዎታል። ለይቶ ማቆያ ውስጥ እያሉ፣ ጠያቂዎች ሊኖርዎት አይችልም። መውጣት ይችላሉ ነገር ግን ሌላ ሰውን መጠየቅ አይችሉም።

የCOVID-19 ክትባት በመጀመሪያ ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እና ምልክቶች ላለባቸው፣ ማለትም በCOVID-19በ ከተያዙ በጣም ሊታመሙ የሚችሉ፣ ሰዎች  እየተሰጠ ይገኛል። ባለስልጣናት ሁሉም አዋቂዎች እንዲከተቡ ከመከሩ፣ አቅርቦቱ ህጋዊ ላልሁኑ አዋቂዎችም የሚተገበር ይሆናል። ክትባቱ ነጻ ነው። ክትባቱ የአጭር ጊዜ የጉንዮሽ ጉዳት ሊያሳድር ይችላል። ከእነዚህም በጣም የተለመዱት፣ በእጅ ላይ ያለ ህምም፣ መለስተኛ የጤንነት የማጣት ስሜት (Malaise)፣ ራስ ምታት እና በተወሰኑ ሁኔታውች ውስጥ ትኩሳት። ይህ ከጥቂት ቀናት በኋላ ይጠፋል።

Innholdet er levert av Helsedirektoratet

Sist oppdatert ማክሰኞ ፣26 ጃንዩወሪ 2021