ወደ ኖርዌይ መግባት - የኳራንታይን እና የምርመራ ደንቦች

ከኖርዌይ ውጭ የ COVID-19 የኢንፌክሽን መጠን በአሁኑ ጊዜ በጣም ከፍተኛ ነው።  ከተወሰኑ የኖርዲክና የአውሮፓ ሀገሮች ክልሎች በስተቀር ከማንኛውም ሀገር ወደ ኖርዌይ ሲመጡ ለ10 ቀናት ወደ ኳራንታይን መግባት አለብዎት።

የተለየ ምክንያት ከሌልዎት በስተቀር፡ በኳራንታይን ጌዜዎ በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ መቆየት ይኖርብዎታል። የድንበር ማቋረጫዎችን እና ሌሎች በኖርዌይ የመዳረሻ ቦታዎች ላይ ስለ የኳራንታይን ሆቴሎች ከፖሊስ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 • የጉዞ መመዝገብያ ቅጽ መሙላት ኣለብዎት
 • አገር ውስጥ ከመግባትዎ በፊት 72 ሰዓታት ባልሞላ ግዜ የተመረመሩበትን ከቫይረሱ ነጻ መሆንዎን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት መያዝ ኣለብዎት
 • ወደ ኖርዌይ ከገቡ በኋላ መመርመር ኣለብዎት
 • በኖርዌይ ለ10 ቀናት ኳረንታይን መሆን ኣለብዎት

በሚገቡበት ወቅት መመዝገብ

ወደ ኖርዌይ የሚገቡ ሁሉ በሚገቡበት ወቅት የሚሞላ ቅጽ በዲጂታል መሙላት አለባቸው። ከዛም ለፖሊስ የምታሳዩት ደረሰኝ ያገኛሉ።

ወደ ኖርወይ ከመድረስዎ በፊት ይመዝገቡ፣ እዚህ ከመድረስዎ ከ72 ሰዓታት በማይበልጥ ግዜ መመዝገብ ኣለብዎት።

በሚገቡበት ወቅት ወደ ምትመዘገብበት የዲጂታል ቅጽ ግባ (entrynorway.no)

ምርመራ

ወደ ኖርዌይ ስትገባ የሚደረግ ኣስገዳጅ ምርመራ

ወደ ኖርዌይ ስትገቡ የግድ መመርመር ኣለብዎት። ባለፉት 14 ቀናት የኳራንታይን ግዴታ ባለባት የውጭ አገር ከነበሩ ወደ ኖርዌይ ከገቡ በኋላ መመርመር ኣለብዎት።

ምርመራው የምደረገው በአውሮፕላን ማረፍያው ወይም በድንበር ማቋረጫዎች መሆን ኣለበት። እዛ ማድረግ ካልቻሉ፡ ሊሄዱ ወዳሰቡበት ማዘጋጃ በመደወል መመርመር ይችላሉ። PCR እና ፈጣን አንቲጂን ምርመራ ተቀባይነት ያላቸው የምርመራ ዘዴዎች ናቸው።

ይህ ምርመራ የኳረንታይን ግዜዎን ለማሳጠር የሚረዳ የመጀመርያ ምርመራ ነው። (ስለ ኳራንታይን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ታች ያንብቡ)

የሚከተሉትን ሰዎች እላይ የተጠቀሰውን ኣስገዳጅ ምርመራ ማድረግ የማያስፈልጋቸው ናቸው፦

 • ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት
 • ተቀባይነት ባለው የምርመራ መንገድ የታወቀ ባለፉት ስድስት ወራት ኮቪድ-19 ይዟቸው እንደ ነበር የሚያሳይ ዶክሜንት ማቅረብ የሚችሉ
 • በአንቀቅ 6ሀ መሰረት በሥራ እና ከስራ ሰዓታት ውጭ ኳራንታይን እንዲገቡ የማይገደዱ
 • ይህ ከስዊድንና ከፊንላንድ እየተመላለሱ ለሚሰሩ ወይም የሚማሩ ሰዎችን ይጨምራል
 • በሙያቸው የረጅም ርቀት የጭነት መኪናዎች አሽከርካሪዎች እና በጭነት ባቡር ላይ የማይሠሩ የባቡር ሠራተኞች
 • ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ ተግባራትን በአግባቡ ለማስፈፀም ወይም ካልገቡ ለሕይወት ወይም ለጤንነት አደጋ የሚጋለጥበት የሕዝቡን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለመከታተል በጣም አስፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎች
 • ዲፕሎማት

የምርመራ ውጤትዎ ኣወንታዊ ከሆነ እንደውልልዎታለን። ኣሉታዊ ከሆነ ግን አንደውልልዎትም። የhelsenorge.no ኣካውን ካልዎት እዛው ገብተው ውጤትዎን ማወቅ ይችላሉ። አንዳድን የምርመራ ማእከላት ከhelsenorge.no በተጨማሪ ውጤትዎን የሚያሳውቁበት መንገድ ስላላቸው በራሳቸው መንገድ ሊያሳውቁህ ይችላሉ።

የCOVID-19 ነጻ የምርመራ ውጤት የምስክር ወረቀት

የኳራንቲን ግዴታ ከተጣለበት ክልል ወደ ኖርዌይ የሚመጡ የውጭ ዜጎች ውጤት የኮሮቫይረስ ምርመራ አድርገው ኔጋቲቭ ውጤታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

 • ምርመራው ወደ ኖርዌይ ከመደረሱ በፊት ባሉት 72 ሰዓታት ውስጥ መወሰድ አለበት
 • PCR እና ፈጣን አንቲጂን ምርመራ ተቀባይነት ያላቸው የምርመራ ዘዴዎች ናቸው
 • የምስክር ወረቀቱ በኖርዌዣን፣ በስዊሲሽ፣ በዳኒሽ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በጀርመንኛ መፃፍ አለበት።

የሚከተሉት ሰዎች የነጻ ምርመራ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አያስፈልጋቸውም

 1. የኖርዌይ ዜጎች
 2. በኖርዌይ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም የመኖሪያ መብት ያላቸው የውጭ ዜጎች
 3. ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ ተግባራትን በአግባቡ ለማስፈፀም ወይም ካልገቡ ለሕይወት ወይም ለጤንነት አደጋ የሚጋለጥበት የሕዝቡን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለመከታተል በጣም አስፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎች
 4. በጉዞ ላይ ያሉ የውጭ ዜጎች
 5. ከኖርዌይ ውጭ ከሰባት ቀናት በላይ ካሳለፉ የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች በስተቀር በመደበኛነት ወደ ስዊድን ወይም ፊንላንድ የሚጓዙ የውጭ ዜጎች
 6. ጥገኝነት ፈላጊዎች እና እንደገና የተቋቋሙ ስደተኞች
 7. ከቤተሰብ ፍልሰት ጋር በተደነገገው መመሪያ መሠረት በኖርዌይ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ዜጎች
 8. በዲፕሎማሲያዊ፣ በውጭ አገልግሎት ወይም በኤምባሲ ግዴታዎች ላይ ያሉ ሰዎች
 9. የተወሰኑ የወታደራዊ ሠራተኞች ቡድን
 10. የውጭ አገር ዜጎች ሸቀጦችን ወይም ተሳፋሪዎችን ማጓጓዝ በሚመለከቱ ሥራዎች ላይ ወይም ወደ ሥራው ሲጓዙ/ሲመለሱ
 11. ወደ ምደባ ወይም ከጉዞ የሚጓዙ አብራሪዎች እና የባህር ተጓዦች
 12. ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች

ከዩናይትድ ኪንግደምና ደቡብ ኣፍሪካ የሚመጡ ሁሉም ተጓዦች

ሲመጡ እና ለ10 ቀናት የኳራንታይን ጊዜን አስመልክቶ ከሚወጣው አጠቃላይ ሕግ በተጨማሪ ከእንግሊዝና ደቡብ ኣፍሪካለሚመጡ ተጓዦች በርካታ መስፈርቶች ቀርበዋል። እነዚህ መስፈርቶች ከ12 ዓመት በላይ ለሆነ ማንኛውም ሰው ይሰራሉ እናም የሚከተለው ናቸው፡

 • PCR ምርመራ (COVID-19 ምርመራ) ወደ ኖርዌይ ከመድረሱ በፊት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ እንግሊዝ ወይም ደቡብ ኣፍሪካ ውስጥ ቆይቶ ኖርዌይ ለሚደርስ ማንኛውም ሰው።

በሚከተሉት ግዜያት መመርመር ይኖርብዎታል፦

 1. መጀመሪያ ላይ በተቻለ ፍጥነት እና ወደ ኖርዌይ ከደረሱ ደግሞ ከ24 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እና ከዚያ በኋላ
 2. ወደ ኖርዌይ ከደረሱ ከ7 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ። የኳራንታይን ጊዜው ከማለቁ በፊት ከ10 ቀናት ባላነሰ ጊዜ ውስጥ ውጤቱ ዝግጁ መሆን አለበት።

እንደ አጠቃላይ ደንብ፣ የመግቢያ የኳራንቲን ነፃነት ከተወሰኑ ድንጋጌዎች በስተቀር ከእንግሊዝ የሚመጡ ተጓዦችን አይመለከትም።

የኳራንታይ

ከተወሰኑ የኖርዲክ አከባቢ/አውሮፓ አካባቢዎች ከሚጓዙት በስተቀር ከውጭ ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ሁሉ ለ10 ቀናት ወደ ኳራንታይን መሄድ አለባቸው  (ቢጫ አካባቢዎች እና ሀገራት)።

በአውሮፓ ውስጥ የቀይ እና ቢጫ ሀገሮች/ክልሎች ካርታ (እንግሊዝኛ ብቻ)

ወደ ኖርዌይ ሲደርሱ በቀጥታ ወደ የኳራንታይን መሄድ አለብዎት፣ እና ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆነ ሁሉ ወደ ኳራንታይን ቦታቸው እስኪደርሱ ድረስ የፊት መሸፈኛ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

አብረው የሚኖሩት እና ወደ ኖርዌይ የመጡ የመግቢያ የኳራንታይን ጊዜያቸውን በአንድ ማረፊያ ውስጥ ሊሚያሳልፉ ይችላሉ።

 • በኳራንታይን ወቅት ሁለት ግዜ ኔጋቲቭ የምርመራ ውጤት ካገኙ የኳራንታይን ግዜዎን ማሳጠር ይችላሉ።የመጀመርያው ምርመራ ኣገር ውስጥ ከገቡ በሶስት ቀን ውስጥ ማድረግ ኣለብዎት። ኣስቸኳይ ምርመራ ወይም የPCR ምርመራ ሊሆን ይችላል።
 • ሁለተኛው ምርመራ ከሰባት ቀናት በኋላ ማድረግ ኣለብዎት። ይሄንን ምርመራ ግን የPCR ምርመራ ብቻ መሆን ኣለበት።

በሁለተኛው ምርመራ ኔጋቲቭ የምርመራ ውጤት እስኪያገኙ ድረስ በኳራንታይን መቆየት ኣለብዎት።

ባለፉት 14 ቀናት በእንግሊዝ አገር ወይም ደቡብ ኣፍሪካ ቆይተው ከነበሩ የመግቢያ የኳራንታይን ጊዜያዎትን ማሳጠር ኣይፈቀድልዎትም።

በኳራንታይን ውስጥ እያሉ የ COVID-19 ምልክቶችን ካሳዩ ራስዎን በማግለል ምርመራን ለማዘጋጀት የአካባቢውን የጤና አገልግሎት ማነጋገር አለብዎት። የስልክ ቁጥር፦ +47 116117

የኳራንታይን ሆቴሎች

ወደ የኳራንቲን የመሄድ ግዴታ ሲኖርብዎት በተለምዶ የኳራንታይን ሆቴል ውስጥ መቆየት ይኖርብዎታል። ይህ ማለት ወደ ኖርዌይ የመጡት ለስራ ወይንም ጓደኞችዎን፣ ቤተሰቦችዎን ወይም አጋርዎን ለማግኘት የመጡ እንደሆን የኳራንታይን ጊዜዎን በኳራንታይን ሆቴል ውስጥ ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል ማለት ነው።

ከኳራንቲን ነፃ ላልሆኑ ልጆች ተንከባካቢዎች በኳራንቲን ሆቴል አብረዋቸው እንዲኖሩ ዝግጅት መደረግ አለበት።

የሚከተሉት ሰዎች በኳራንታይን ሆቴል ውስጥ መቆየት አያስፈልጋቸውም

 1. በኖርዌይ ነዋሪ የሆኑ (በብሔራዊ የሕዝብ ምዝገባ መዝገብ የተመዘገቡ) ወይም በኖርዌይ ውስጥ ቋሚ መኖሪያ መኖራቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ (ለምሳሌ በኖርዌይ የግብር አስተዳደር ወይም በተከራይ እና አከራይ ውል የተመዘገበ መኖሪያ)።
 2. በኳራንታይናቸው ወቅት የሚቆዩበት ተስማሚ ቦታ እንዳላቸው ማረጋገጥ የሚችሉ። ‘ተስማሚ ቦታ’ ማለት ከአንድ ክፍል ጋር ማረፊያ፣ የግል መታጠቢያ ቤት፣ የራሱ የሆነ ወጥ ቤት ወይም የምግብ አገልግሎት የሚገኝበት ቦታ ሲሆን ከሌሎች ሰዎች ጋር ቅርበት እንዳይኖር ማድረግ የሚቻልበት። ይህ ለምሳሌ ለሰውየው በጊዜያዊነት የተሰጠ የበዓል ቤት፣ ሆቴል ወይም ሌላ ማረፊያ ሊሆን ይችላል።
 3. በኖርዌይ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካለው ሰው ጋር የተጋቡ ወይም የጋራ ልጆች የነበራቸው ሰዎች እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቻቸው። እነዚህ ሰዎች ባለቤታቸው ወይም በሌላ ወላጅ መኖሪያ ውስጥ የኳራንቲን ጊዜያቸውን ማጠናቀቅ ይችላሉ።
 4. አሰሪው ወይም ደንበኛው በአንድ ክፍል ውስጥ ተስማሚ ማረፊያ የሚያመቻቹ የንግድ ተጓዦች። ሥራ ወይም ተልእኮ ለመፈፀም እንዳሰቡ እና አሠሪዎ ወይም ደንበኛዎ ተስማሚ ማረፊያ እንዳዘጋጀልዎት ማረጋገጫ ሊኖርዎት ይገባል። 'ተስማሚ ማረፊያ' ከሌሎች ሰዎች ጋር ቅርርብ ላለመፍጠር የሚቻልበት ቦታ ነው፣ አንድ ክፍል ቴሌቪዥን እና የበይነመረብ መዳረሻ ያለው የግል ክፍል፣ የግል መታጠቢያ ቤት፣ የራሱ የሆነ ወጥ ቤት ወይም የምግብ አገልግሎት ያለው፣ ማስረጃው ለምሳሌ የሥራ ውል ሊሆን ይችላል ወይም የምደባ ስምምነት እና የመኖሪያ ቦታውን ከሚገልጽ ከአሰሪ የተሰጠ መግለጫ። መግለጫው የት እንደሚቆዩ እንዲሁም የአሰሪውን ወይም የደንበኛውን ስም፣ አድራሻ እና የስልክ ቁጥር ማስፈር አለበት።
 5. ጥገኝነት ፈላጊዎች እና እንደገና የተቋቋሙ ስደተኞች።
 6. የኳራንቲን ጊዜያቸውን ለመኖርያ በሚመች ተሽከርካሪ ወይም ባቡር ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ ማሳለፍ ከቻሉ በጭነት ባቡር ላይ የማይሠሩ የባለሙያ የረጅም ርቀት የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የባቡር ሠራተኞች።
 7. በኖርዌይ መከላከያ ሚኒስቴር ለፀደቀው ስልጠና፣ ልምምዶች ወይም ሥራዎች ወደ ኖርዌይ የሚመጡ የውጭ ወታደራዊ ክፍፍሎች።
 8. የኖርዌይ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች ማጥናት ከመጀመራቸው በፊት በኖርዌይ የህዝብ ምዝገባን አስመልክቶ በልዩ የኖርዲክ ህጎች ምክንያት በትምህርቱ ሀገር ለመኖር የተመዘገቡትን ጨምሮ በኖርዌይ ብሔራዊ የህዝብ ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ናቸው። በኳራንታይኑ ወቅት የኳራንቲን ጊዜው ከመጀመሩ በፊት ከማይኖሩባቸው ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነትን ማስወገድ አለባቸው።

ነፃነቶቹ በኳራንታይኑ ወቅት በመኖሪያ ቤትዎ ወይም ተስማሚ በሆነ መጠለያዎ ውስጥ እንደሚቆዩ ያስባሉ።

ወጪዎች

በኳራንቲን ሆቴል የሚከፈለው የግል መዋጮ ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ለግለሰቦች እንዲሁም ለአሰሪዎች በቀን NOK 500 ነው። ከ10 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት  ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ የሚቆዩ ምንም ክፍያ አይከፈልም።  ከ10 እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች ግማሹን የግል መዋጮ ማለትም በየቀኑ NOK 250 ይከፍላሉ። ሲመጡም ሆነ ሲወጡ በፊት የግል መዋጮው በተለመደው መንገድ በኳራንታይን ሆቴል መከፈል አለበት።

የ COVID-19 ምርመራዎች በኳራንቲን ሆቴል ውስጥ በነፃ ይሰጣሉ።

ለሰራተኞች የመግቢያ የኳራንታይን

አጠቃላይ ደንቡ የሚለው ወደ ኖርዌይ ሲደርሱ ወደ ኳራንታይን መሄድ አለብዎት ነው፣ ነገር ግን አንዳንድ የተለዩ ሁኔታዎች አሉ። አንዳንድ የተለዩ ሁኔታዎች በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ ላይ የሚውሉ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በሥራ ሰዓት ብቻ ይተገበራሉ።

ከፍተኛ የስርጭት መጠን ካለባቸው ከማናቸውም ሃገራት ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ሰዎች በሙሉ: 

 • ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለ 10 ቀናት በኳራንታይን ውስጥ መግባት አለባቸው
 • ኣስቀድሞ በተገለጸው መሰረት ሁለት ግዜ ነጋቲቭ የምርመራ ውጤት ካገኙ የኳረንታይን ግዜዎትን ማሳጠር ይችላሉ

ዝቅተኛ የመያዝ መጠን ካላቸው ከአንዳንድ የኖርዲክ ክልል/አውሮፓ አካባቢዎች (ኢንግሊዝኛ ብቻ)

በስራ ሰዓታት ኳራንታይን መግባት ግዴታ የሌለባቸው አንዳንድ ሰራተኞች

በEEA ወይም በስዊዘርላንድ ውስጥ የኳራንታይን ግዴታ ካለባቸው የውጭ አገር ሠራተኛ ከሆኑ ወይም በኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ እና እነዚህን ሀገሮች ለስራ ዓላማ ወይም ለተመደቡበት ስራ የጎበኙ እንደሆነ ፡

 • ኔጋቲቭ ምርመራ እስኪያደርጉ ድረስ በኳራንቲን ውስጥ መቆየት አለብዎት
 • በኖርዌይ ውስጥ ከተወሰደው የመጀመሪያ ኔጋቲቭ ምርመራዎ በኋላ ሥራ መጀመር ይችላሉ፣ ነገር ግን በየሶስት ቀናት ለ10 ቀናት ምርመራ ማድረግ እና ከመጡ በኋላ ለ10 ቀናት ከስራ ሰዓት ውጭ በኳራንታይን ውስጥ መቆየት አለብዎትለኳራንታይን ጊዜው በአንድ ክፍል ውስጥ መቆየት አለብዎት (በኖርዌይ የሚኖሩ እና ከEEA ወይም ስዊዘርላንድ ከሥራ ወይም ንግድ የሚመለሱትን አይመለከታቸውም)።

ወደ ኖርዌይ ከመምጣትህ በፊት በነበሩ 10 ቀናት ከፍተኛ የኢንፌክሽን መጠን ባለበት አገር ቆይተህ ከነበረ ከላይ የተጠቀሰውን ላንተ ኣይሰራም።

በEEA/ስዊዘርላንድ ውስጥ ያሉ የኳራንታይን ግዴታ ያለባቸው ነገር ግን ለሠራተኞች ነጻነት የተሰጠባቸው ሀገሮች እና ክልሎች፣ በካርታው ላይ ቀይ ሀገሮች (በእንግሊዝኛ ብቻ)።

ዝቅተኛ የመያዝ መጠን ካላቸው ከኖርዲክ ሀገሮች ውስጥ ከሚገኙ የተወሰኑ ክልሎች የሚመጡ ከሆነ ከኳራንታይን ግዴታ ነፃ ይሆናሉ።

በበቂ ሁኔታ ዝቅተኛ የመያዝ መጠን ያላቸው ሐገራት እና ክልሎች (እንግሊዝኛ ብቻ)

ተጓዦችን እና ድንበሩን በተደጋጋሚ የሚያቋርጡ ሰዎች

 • በ 15-ቀናት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ የኳራንታይን ግዴታ ከተጣለባቸው ከስዊድን ወይም ከፊንላንድ ክፍሎች ወደ ኖርዌይ ድንበር የሚያቋርጡ ሰዎች፣ በመጨረሻ SARS-CoV-2 ከተመረመሩበት ጊዜ ሰባት ቀን ካለፋቸው፣ በመጡበት ቀን እና በየሰባት ቀናት በኖርዌይ ውስጥ ራሳቸውን ካስመረመሩ ከኳራንታይን ነፃ ይሆናሉ።
 • ከነዚህ መካከል በሙያቸው የረጅም ርቀት የጭነት መኪና ሹፌሮች፣ የባቡር ሠራተኞች እና የአየር መንገድ ሠራተኞች ከጉዞ የኳራንታይን ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማወቅ ከአሰሪዎቻቸው ጋ ይነጋገሩ።
 • ተጨማሪ ያንብቡ (እንግሊዝኛ ብቻ)

የሚከተሉት ሰዎች በሥራ እና ከስራ ሰዓታት ውጭ ከመግቢያ የኳራንታይን ሙሉ በሙሉ ነፃ ናቸው፡

 • በፒሲአር ምርመራ ወይም በፈጣን አንቲጂን ምርመራ እንደተረጋገጠው ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ COVID-19 መያዛቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ሰዎች።
 • ወደ ኖርዌይ የሚጓዙ ሰዎች ለመገናኘት የተስማሙ ወይም ያዘጋጁ ወላጆች እና ልጆች። ወደ ውጭ ውጪ ሄደው ወደ ኖርዌይ ለሚመለሱ ሰዎች ተመሳሳይ ነው።
 • ከውጭ ፖሊሲ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች በኖርዌይ የመንግስት ባለስልጣን የተጋበዙ ሰዎች።
 • ሰዎች በጠና የታመመ የቅርብ ዘመድ ለመጠየቅ፣ ወይም የቅርብ ዘመድ ሬሳ ማቃጠል ወይም የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመከታተል ከገቡ የኳራንቲን አገልግሎት ጊዜ ሊሰጥላቸው ይችላል። ከኳራንታይን ነፃ መሆን ተፈጻሚ የሚሆነው የታመመውን ሰው ሲጎበኙ ወይም አስከሬኑ/የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሚከታተሉበት ጊዜ ብቻ ይሆናል። ከዚህ ውጪ ባለው የኳራንታይን ግዴታው ፈጻሚ ነው። በማዘጋጃ ቤቱ ውስጥ ዋና የሕክምና ባለሙያ እንደዚህ ዓይነቶቹን ነፃነቶች የመስጠት ኃላፊነት አለበት።

ከኳራንቲን ግዴታው ነፃ ከሆኑ እና የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታየብዎ ወይም ሀኪም በኮቪድ-19 ተይዘው እንደሆን ከጠረጠሩ አሁንም ወደ ኳራንታይን መግባት አለብዎት።

የሥራ ዘመን የተሰጣቸው ሰዎች በሚቻልበት ቦታ ሁሉ ኮቪድ-19 መመርመር አለባቸው።

የመግቢያ የኳራንቲን ምን ምን ያካትታል

 • ከላይ በተጠቀሰው ዝርዝር እንደተገለፀው ከኳራንታይን ሆቴል ነፃ የመሆን መብት ከተሰጠዎት የኳራንታይን አገልግሎት በኳራንታይን ሆቴል ወይም በሌላ ተስማሚ ቦታ ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል።
 • እርስዎ ጋር ካሉ ሰዎች ውጪ የቅርብ ግንኙነትን ለማስወገድ ከቻሉ ብቻ የሚቀመጡበትን ቦታ ለቀው መውጣት ይችላሉ።
 • ሌሎች ሰዎች በሚገኙባቸው ማናቸውም የሥራ ቦታዎች፣ ትምህርት ቤቶች ወይም መዋለሕፃናት መገኘት የለብዎትም።
 • ወደ ኖርዌይ ከመግባትዎ/ከመነሳትዎ ጋር በተያያዘ ከአውሮፕላን ማረፊያ፣ ወደብ ወይም ከሌላ ወይም ወደ ሌላ ተመሳሳይ ስፍራ ለመጓዝ ካልሆነ በቀር በሕዝብ ማመላለሻ መጓዝ የለብዎትም። በዚህ ሁኔታ ዕድሜዎ ከ12 ዓመት በላይ ከሆነ የፊት መሸፈኛ ማጥለቅ አለብዎ።

ስለ ኮሮና ቫይረስ ተጨማሪ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች እዚህ ያገኛሉ (regjeringen.no)

ለበለጠ መረጃ፣ helsenorge.no/coronavirus ይመልከቱ

ይዘቱ የሰራው በ The Norwegian Directorate of Health / Innholdet er levert av Helsedirektoratet ነው